عَنْ عَلِيٍّ رضي الله عنه قَالَ:
كُنْتُ رَجُلًا مَذَّاءً وَكُنْتُ أَسْتَحْيِي أَنْ أَسْأَلَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِمَكَانِ ابْنَتِهِ فَأَمَرْتُ الْمِقْدَادَ بْنَ الْأَسْوَدِ فَسَأَلَهُ فَقَالَ: «يَغْسِلُ ذَكَرَهُ وَيَتَوَضَّأُ». وَلِلبُخَاريِّ: فَقَالَ: «تَوَضَّأْ وَاغْسِلْ ذَكَرَكَ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከዐሊ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ አፈርኩና ሚቅዳድ ቢን አስወድን እንዲጠይቃቸው አዘዝኩት፤ ጠየቃቸው። እርሳቸውም 'ብልቱን ይታጠብና ዉዱእ ያድርግ።' አሉ።" በቡኻሪ ዘገባ ደሞ "ዉዱእ አድርግ፤ ብልትህንም እጠብ።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መዚይ (ነጭ፣ ቀጭን፣ የሚዝለገለግ፣ ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት ወይም ከግንኙነት በፊት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) ብዙ ጊዜ ይወጣቸው እንደነበር ተናገሩ። መውጣቱን ተከትሎ እንዴት ማድረግ እንዳለባቸውም አያውቁም። የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልጅ ፋጢማ ባለቤት ስለሆኑ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጠየቅ አፈሩ። ሚቅዳድ ቢን አስወድ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለዚህ ጉዳይ እንዲጠይቅላቸው አድርገው ላኩት። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ብልቱን አጥቦ ዉዱእ ማድረግ እንደሚገባው በመንገር መልስ ሰጡት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አይነ አፋርነቱ በሰው አማካኝነት እንኳ ከማስጠየቅ አለማቀቡ የዐሊይ ቢን አቢጧሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ ያስረዳናል።
  2. ፈትዋ ለመጠየቅ ሰው መተካት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  3. አንድ ሰው ስለራሱ የሚያሳፍር ነገርንም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ መናገሩ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  4. የመዚይን ነጃሳነትና ከሰውነትም ከልብስም ላይ ማጠብ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  5. የመዚይ መውጣት ዉዱእን ከሚያፈርሱ ነገሮች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
  6. ብልትንና ሁለቱን ፍሬዎች ማጠብ እንደሚገባ የሚያዝ ሌላ ሐዲሥ ስላለ ብልትንና ሁለቱን ፍሬዎች ማጠብም ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ተጨማሪ