عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنه:
أَنَّهُ لَقِيَهُ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي طَرِيقٍ مِنْ طُرُقِ الْمَدِينَةِ وَهُوَ جُنُبٌ، فَانْسَلَّ فَذَهَبَ فَاغْتَسَلَ، فَتَفَقَّدَهُ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَلَمَّا جَاءَهُ قَالَ: «أَيْنَ كُنْتَ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ؟» قَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، لَقِيتَنِي وَأَنَا جُنُبٌ فَكَرِهْتُ أَنْ أُجَالِسَكَ حَتَّى أَغْتَسِلَ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «سُبْحَانَ اللهِ، إِنَّ الْمُؤْمِنَ لَا يَنْجُسُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 371]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«ከመዲና መንገዶች በአንዱ መንገድ ላይ እርሱ ጀናባ ላይ ሆኖ ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲያገኙት ከእይታቸው ተደብቆ በመሄድ ገላውን ታጠበ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፈልገው አጡት። በሚመጣበት ወቅትም "አቡ ሁረይራ ሆይ! የት ነበርክ?" አሉት። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔን ያገኙኝ ጀናባ ላይ ሆኜ ስለነበር ገላዬን ሳልታጠብ ከርሶ ጋር መቀማመጥን ጠላሁ።" አላቸው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱብሓነላህ! ሙእሚን'ኮ ነጃሳ አይሆንም።" አሉት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 371]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ የመዲና መንገድ ላይ አቡ ሁረይራን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አገኙ። አቡ ሁረይራም ጀናባ (የዘር ፈሳሽ ወጥቶት ገላውና ያልታጠበ) ላይ ስለነበር ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከነበረው ክብርና ልቅና የተነሳ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከርሳቸው ጋር መቀማመጡንና ማውራቱን ጠላ። ተደብቆ በመሄድም ታጠበና ከዚያም ተመልሶ መጣና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የት ሄዶ እንደነበር ጠየቁት። የነበረበትንም ሁኔታ ነገራቸው። እርሱ በጀናባ ምክንያት ተነጅሶ ስለነበር ከርሳቸው ጋር መቀማመጥ ጠልቶ መሆኑን ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመደነቅ እንዲህ አሉት: አማኝ ሰው በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን በሕይወትም ሆነ ሞቶ ንፁህ ነው አይነጀስም።