عن عَبْدِ اللهِ بْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ:
«مَنْ جَاءَ مِنْكُمُ الْجُمُعَةَ فَلْيَغْتَسِلْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 894]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው:
"ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 894]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጁሙዓን ሶላት ለመስገድ የሚመጣ ሰው ለጀናባ እንደሚታጠበው ትጥበት አምሳያ መታጠብ ለርሱ ተወዳጅ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው ተናገሩ።