የሓዲሦች ዝርዝር

ከጀናባ አስተጣጠብ ሁኔታ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ