የሓዲሦች ዝርዝር

አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ተረከዞቻችሁን ከእሳት አድኑ! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከጀናባ አስተጣጠብ ሁኔታ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ አፈርኩና ሚቅዳድ ቢን አስወድን እንዲጠይቃቸው አዘዝኩት፤ ጠየቃቸው። እርሳቸውም 'ብልቱን ይታጠብና ዉዱእ ያድርግ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'በእጅህ እንዲህ ብታደርግ በቂህ ነበር።' አሉና ከዚያም በሁለት እጃቸው መሬቱን አንድ ጊዜ መቱ። ከዚያም በግራ እጃቸው ቀኝ እጃቸውን አበሱ። የላይኛውን የመዳፋቸው ክፍልንና ፊታቸውን አበሱ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ" በማለት መለሰችልኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ የተኛ ጊዜ በማጅራቱ ላይ ሸይጧን ሶስት ቋጠሮ ይቋጥራል። በየሁሉም ቋጠሮ ላይም ረጅም ሌሊት አለና ተኛ! እያለ ይመታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ውሃው ሁለት 'ቁለተይን' ከደረሰ ነጃሳን አይሸከምም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'አንድ ሰውዬ ውዱእ አደረገና እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል ስፍራ ተወ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተመለከቱትና እንዲህ አሉት: ‹ተመለስና ዉዱእህን አሳምር!› ተመልሶ (አስተካከለና) ከዚያም ሰገደ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዹእ ያደርጉ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዉዱኡን አሳምሮ የሚያደርግና ከዚያም በቀልቡም በፊቱም ወደ አላህ ተመልሶ ቆሞ ሁለት ረከዓ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም ለርሱ ጀነት ግዴታ (ተገቢ የሆነች) ብትሆንለት እንጂ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ዉዱእ አድርጎ ኹፎቹን የለበሰ እንደሆነ እነርሱን እንደለበሰ ይስገድ። በነርሱም ላይ ያብስና ከዚያም ለጀናባ ካልሆነ በቀር ከፈለገ አያውልቃቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ አድርገዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ) ከመስጂድ አይውጣ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት የወጡ ጊዜ "ጉፍራነክ" ይሉ ነበር።» (ትርጉሙም "ምህረትህን እለምንሃለሁ" ማለት ነው።)
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ