عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤمنين رضي الله عنها أَنَّ فَاطِمَةَ بِنْتَ أَبِي حُبَيْشٍ سَأَلَتِ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَتْ:
إِنِّي أُسْتَحَاضُ فَلاَ أَطْهُرُ، أَفَأَدَعُ الصَّلاَةَ؟ فَقَالَ: «لَا، إِنَّ ذَلِكِ عِرْقٌ، وَلَكِنْ دَعِي الصَّلاَةَ قَدْرَ الأَيَّامِ الَّتِي كُنْتِ تَحِيضِينَ فِيهَا، ثُمَّ اغْتَسِلِي وَصَلِّي».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው ፋጢማ ቢንት አቢ ሑበይሽ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ በማለት ጠየቀች:
" 'እኔ የበሽታ ደም ይፈሰኛልና አልፀዳም። ሶላት ልተውን?' እርሳቸውም 'በፍፁም! ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ፋጢማ ቢንት ሑበይሽ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): "እኔ የሚፈሰኝ ደም ከወር አበባ ጊዜዬም ውጪ መፍሰሱ አልቋረጥ አለ። ታዲያ የዚህ ደም ብይን እንደ ወር አበባ ደም ብይን ነውን? ሶላትንስ ልተውን?" በማለት ጠየቀች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሏት: "ይህ በማህፀን ውስጥ የሚገኝ ደም ስር በመቆረጡ ሳቢያ የሚመጣ የበሽታ ደም እንጂ የወር አበባ ደም አይደለም። በበሽታ ደም ከመታመምሽ በፊት በወርሃዊ ልምድሽ የወር አበባን ታይበት የነበርሽበትን የጊዜ መጠን ልክ ሲመጣ ሶላት፣ ፆምና ሌሎችንም የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በወር አበባ ወቅት የምትከለከላቸውን ነገሮች ተይ! የወር አበባ ቀናትሽ መጠን በተጠናቀቀ ጊዜ ከወር አበባ ነፅተሻልና የደሙን ስፍራ እጠቢ ከዚያም ሐደሥሽን (ከሶላት የከለከለሽን) ለማስወገድ ሰውነትሽን ሙሉ ትጥበት ታጥበሽ ከዚያም ስገጂ።" አሏት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሴት ልጅ የወር አበባ ቀናቷ በሚጠናቀቅበት ወቅት መታጠብ ግዴታዋ መሆኑን እንረዳለን።
  2. የበሽታ ደም በሚፈሳት ላይም ሶላት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  3. የወር አበባ ማለት: ተፈጥሯዊ ደም ሲሆን የደረሰች ሴት ማህፀን በብልት በኩል የሚለቀው ደም ነው። የሚከሰትባትም በታወቁ ቀናት ውስጥ ነው።
  4. የበሽታ ደም ማለት: ያለ ወቅቱ ከማህፀን ጥልቁ ክፍል ሳይሆን ከማህፀን አቅራቢያ ክፍል የሚፈስ ደም ነው።
  5. በወር አበባና በበሽታ ደም መካከል ያለው ልዩነት: የወር አበባ ደም ጥቁር፣ ወፍራምና ሽታው የሚከረፋ ነው። የበሽታ ደም ግን ቀይ፣ ቀጭንና የሚከረፋ ሽታም የሌለው ነው።