+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنينَ رَضي الله عنها أَنَّهَا قَالَتْ:
إِنَّ أُمَّ حَبِيبَةَ بِنْتَ جَحْشٍ الَّتِي كَانَتْ تَحْتَ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ عَوْفٍ شَكَتْ إِلَى رَسُولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم الدَّمَ، فَقَالَ لَهَا: «امْكُثِي قَدْرَ مَا كَانَتْ تَحْبِسُكِ حَيْضَتُكِ، ثُمَّ اغْتَسِلِي». فَكَانَتْ تَغْتَسِلُ عِنْدَ كُلِّ صَلَاةٍ.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 334]
المزيــد ...

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"የዐብዱረሕማን ቢን ዐውፍ ባለቤት የነበረችው ኡሙ ሐቢባ ቢንት ጀሕሽ የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለምታየው ደም ስሞታ አቀረበች። እርሳቸውም 'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።' አሏት። እርሷም ለሁሉም ሶላት ትታጠብ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 334]

ትንታኔ

አንዲት ሶሐቢያ ደሟ ሳይቋረጥ መፍሰሱን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጥታ ስሞታ አቀረበች። ይህ ነገር ከመከሰቱ በፊት የወር አበባዋ የሚያግዳትን ቀናት ያክል ሶላት ከመስገድ እንድታቋርጥና ከዚያም ታጥባ እንድትሰግድ አዘዟት። በራሷ ተነሳሽነትም ለሁሉም ሶላት ትታጠብ ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የበሽታ ደም ማለት: ከተለመደው የወር አበባ ቀናት በኋላ በሴት ልጅ ላይ ደም መውጣቱ መቀጠሉ ነው።
  2. የበሽታ ደም የሚወጣት ሴት: አሁን ያጋጠማት የበሽታ ደም ከመከሰቱ በፊት የወር አበባ ይወጣት የነበሩትን ቀናት ያክል ራሷን የወር አበባ ላይ እንዳለች አድርጋ መቁጠር ይገባታል።
  3. መጀመሪያ የለመደችው የወር አበባ ቀናቶች ካለፈ በኋላ የበሽታ ደሟ አብሯት ቢሆንም እንኳ ልክ ራሷን ከወር አበባ እንደፀዳች አድርጋ ትቆጠራለች። ከወር አበባዋም ትታጠባለች።
  4. የበሽታ ደም ላይ ያለች ሴት ለሁሉም ሶላት የመታጠብ ግዴታ የለባትም። የሶሐቢዯ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና መታጠብ በራሷ ጥረት ነው። ግዴታ ቢሆን ኖሮ የአላህ መልክተኛ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያብራሩላት ነበር።
  5. የበሽታ ደም ላይ ያለች ሴት ለሁሉም ሶላት ዉዱእ ማድረግ ግዴታዋ ነው። የርሷ ሐደሥ የማይቋረጥ ዘውታሪ ነውና። ልክ እንደርሷ ሁሉ ሽንቱን የማይቆጣጠር ወይም ሳይቋረጥ ፈስ የሚወጣውንም ይካትታል፤ ሐደሡ ዘውታሪ የሆነ ሰው ሁሉ ለሁሉም ሶላት ዉዱእ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
  6. ይህቺ ሴት ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመምጣት የሚያጋጥማትን የደም መብዛት መጠየቋ አስቸጋሪ ለሆኑ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የእውቀት ባለቤቶችን መጠየቅ እንደሚገባ ያስረዳናል።