عن أُمِّ عَطِيَّةَ رَضي الله عنها، وكَانَتْ بايَعَت النبيَّ صلى الله عليه وسلم، قالت:
كُنَّا لا نَعُدّ الكُدرَةَ والصُّفْرَةَ بعدَ الطُّهرِ شيئًا.
[صحيح] - [رواه أبو داود بهذا اللفظ، ورواه البخاري بدون زيادة (بعد الطهر)] - [سنن أبي داود: 307]
المزيــد ...
ከኡሙ ዐጢያህ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው: ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቃልኪዳን ተጋብታ ነበር። እንዲህ አለች:
"ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ በዚሁ ቃል ሲዘግቡት ቡኻሪ ደግሞ (ከመፅዳት በኋላ) ከሚለው ጭማሪ ውጪ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 307]
ሶሐቢዯ ኡሙ ዐጢየህ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና-በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘመን የነበሩ ሴቶች ከወር አበባ መፅዳትን ካዩ በኋላ ቀለሙ ወደ ጥቁር ወይም ወደ ዳለቻ ያዘነበለ ከብልት የሚወጣውን ፈሳሽ የወር አበባ አድርገው እንደማይቆጥሩትና ለርሱ ብለውም ሶላትና ፆም እንደማይተዉ ተናገረች።