عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ: خَرَجَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي أَضْحَى أَوْ فِطْرٍ إِلَى المُصَلَّى، فَمَرَّ عَلَى النِّسَاءِ، فَقَالَ:
«يَا مَعْشَرَ النِّسَاءِ، تَصَدَّقْنَ، فَإِنِّي أُرِيتُكُنَّ أَكْثَرَ أَهْلِ النَّارِ» فَقُلْنَ: وَبِمَ يَا رَسُولَ اللَّهِ؟ قَالَ: «تُكْثِرْنَ اللَّعْنَ، وَتَكْفُرْنَ العَشِيرَ، مَا رَأَيْتُ مِنْ نَاقِصَاتِ عَقْلٍ وَدِينٍ أَذْهَبَ لِلُبِّ الرَّجُلِ الحَازِمِ مِنْ إِحْدَاكُنَّ»، قُلْنَ: وَمَا نُقْصَانُ دِينِنَا وَعَقْلِنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ؟ قَالَ: «أَلَيْسَ شَهَادَةُ المَرْأَةِ مِثْلَ نِصْفِ شَهَادَةِ الرَّجُلِ» قُلْنَ: بَلَى، قَالَ: «فَذَلِكِ مِنْ نُقْصَانِ عَقْلِهَا، أَلَيْسَ إِذَا حَاضَتْ لَمْ تُصَلِّ وَلَمْ تَصُمْ» قُلْنَ: بَلَى، قَالَ: «فَذَلِكِ مِنْ نُقْصَانِ دِينِهَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 304]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዒድ አልአድሓ ወይም በዒድ አልፈጥር ወደ መስገጃ ስፍራ ሲሄዱ በሴቶች በኩል አለፉና እንዲህም አሉ:
"እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ። ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዲናችንና አይምሯችን መጉደል ምንድን ነው?" አሉ። እርሳቸውም "የአንድ ሴት ልጅ ምስክር እንደ ግማሽ የወንድ ምስክር አይደለም የሚቆጠረው?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የአይምሮዋ መጉደሉ ነው። የወር አበባ ባየች ጊዜ አትሰግድምም አትጾምም አይደል?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የዲናቸው መጉደሉ ነው።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 304]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዒድ ቀን ወደ መስገጃ ስፍራ ወጡ። ሴቶችን ለብቻቸው ሊገስጿቸው ቃል ገብተውላቸው ነበር። የዛን ቀን ቃላቸውን አሳኩ። እንዲህም አሏቸው: እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! ምህረት መጠየቅንም አብዙ! እነርሱ ከትላልቅ ወንጀል ማስማሪያዎች መካከል ናቸው። እኔ ወደ ሰማይ ባረግኩበት ምሽት አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ ተመልክቻችኋለሁና።
ከነርሱ መካከል የሆነች አንድ አስተውሎት፣ ብስለትና እርጋታን የተላበሰች ሴትም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ለምንድነው አብዛኛው የእሳት ነዋሪ የሆንነው?" አለች።
እርሳቸውም አሉ: ለብዙ ምክንያቶች ነው: እርግማንና ስድብ ታበዛላችሁ፣ የባል ሐቅን ትክዳላችሁ። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴቶችን "አይምሮና ዲን የጎደለባቸው ሆነው የአይምሮ፣ የአስተሳሰብ፣ የቆራጥነት ባለቤት የሆነና ጉዳዩን የሚወስን የሆነን ወንድ የሚያሸንፍ እንደናንተ አልተመለከትኩም።" ብለው ገለጿቸው።
እርሷም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የአይምሮና ዲን መጉደል ምንድን ነው?" አለች።
እርሳቸውም "የአይምሮ መጉደልማ የሁለት ሴት ምስክርነት የአንድ ወንድ ምስክርነት ጋር ይስተካከላል። ይህ የአይምሮ ጉድለታችሁ ነው። የዲናችሁ መጉደል ደግሞ ቀናቶችና ምሽቶችን በወር አበባ ምክንያት ሳትሰግድና ጾሟን ትታ እያፈጠረች በመቆየቷ መልካም ስራን ማጓደሏ ነው። ነገር ግን እነርሱ በዚህ ምክንያት አይወቀሱምም አይጠየቁምም። ምክንያቱም የሰው ልጅ ገንዘብ በመውደድ፣ በመቸኮል፣ በመሃይምነትና ከዚህም ውጪ ባሉ ነገሮች ላይ ሆኖ እንደተፈጠረው ሁሉ ይህም የሴቶች ተፈጥሯቸው ነውና። ይህን ያስገነዘቡትም በነርሱ ከመፈተን እንድንጠነቀቅ ነው።