+ -

عَنْ بُرَيْدَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ حَلَفَ بِالْأَمَانَةِ فَلَيْسَ مِنَّا».

[صحيح] - [رواه أبو داود وأحمد] - [سنن أبي داود: 3253]
المزيــد ...

ከቡረይዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 3253]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአደራ ከመማል ከለከሉም አስጠነቀቁም። ይህን ድርጊት የፈፀመም ከኛ አይደለም አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከአላህ ውጪ መማል ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ከዚህም መካከል በአደራ መማል አንዱ ነው። ይህም ከትንሹ ሺርክ መካከል ነው።
  2. አማና የምትለዋ ቃል ትእዛዝን፣ አምልኮን፣ አደራን፣ ገንዘብንና ደህንነትን የሚጠቀልል የወል ስም ነው።
  3. መሃላ በአላህ ወይም ከስሞቹ መካከል በአንድ ስሙ ወይም ከባህሪያቶቹ መካከል በአንድ ባህሪው ካልሆነ በቀር አይታሰርም።
  4. ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ክልከላ የመጣው እርሳቸው በአላህና በባህሪያቱ እንዲምል ስላዘዙ ይመስላል። አደራ ደሞ ከአላህ ባህሪያቶች መካከል ሳይሆን ከትእዛዞቹ መካከል አንድ ትእዛዙ፣ ከግዴታዎቹ መካከል አንዱ ግዴታው ነው። ከዚህ የተከለከሉትም በርሷ መካከልና በአላህ ስምና ባህሪያት መካከል እኩል ማድረግ ስለሚሆን ነው።"