عَنْ مَحْمُودِ بْنِ لَبِيدٍ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ أَخْوَفَ مَا أَخَافُ عَلَيْكُمُ الشِّرْكُ الْأَصْغَرُ» قَالُوا: وَمَا الشِّرْكُ الْأَصْغَرُ يَا رَسُولَ اللهِ؟ قَالَ: «الرِّيَاءُ، يَقُولُ اللهُ عز وجل لَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ إِذَا جُزِيَ النَّاسُ بِأَعْمَالِهِمْ: اذْهَبُوا إِلَى الَّذِينَ كُنْتُمْ تُرَاؤُونَ فِي الدُّنْيَا، فَانْظُرُوا هَلْ تَجِدُونَ عِنْدَهُمْ جَزَاءً؟».
[حسن] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 23630]
المزيــد ...
ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺርክ ነው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሺርክ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ። እሳቸውም "ይዩልኝ ነው። የትንሳኤ ቀን ሰዎች በስራዎቻቸው የተመነዱ ጊዜ ለነርሱ አሸናፊውና የላቀው አላህ እንዲህ ይላቸዋል፦ 'እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ?' "
[ሐሰን ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 23630]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ላይ እጅግ የሚፈሩት ነገር ትንሹን ሺርክ እንደሆነ እሱም ይዩልኝ እንደሆነ ተናገሩ። ይሀውም ለሰዎች ብሎ መስራቱ ነው። ቀጥለውም ለይዩልኝ የሚሰሩ ሰዎች የትንሳኤ ቀን የሚጠብቃቸውን ቅጣት ተናገሩ። ለነርሱ: "እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ? ለዚህ ስራችሁ ለናንተ መመንዳትና አጅር መስጠት ይችላሉን?" እንደሚባሉም ተናገሩ።