عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم:
«اللهُمَّ لَا تَجْعَلْ قَبْرِي وَثَنًا، لَعَنَ اللهُ قَوْمًا اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ».
[صحيح] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 7358]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡
"አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 7358]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቀብራቸውን በማላቅና የሱጁድ አቅጣጫውን ወደዛው በማድረግ ሰዎች ቀብራቸውን እንደሚያመልኩት ጣኦት እንዳያደርግባቸው አምላካቸውን ተማፀኑ፤ ከዚያም የነቢያቶችን መቃብር የአምልኮ ስፍራ አድርገው በሚይዙ ላይ የአሏህ እርግማን እንደሰፈነባቸውና ከእዝነቱም እንዳባረራቸው አሳወቁ። ምክንያቱም መቃብሩን የአምልኮ ስፍራ አድርጎ መያዝ የቀብሩን ባለቤት እንዲመለክ ለማድረግና በተቀበረበት አካል ዙርያ አጉል እምነት ለማሳደር መዳረሻ ነውና።