عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَثَلُ القَائِمِ عَلَى حُدُودِ اللَّهِ وَالوَاقِعِ فِيهَا، كَمَثَلِ قَوْمٍ اسْتَهَمُوا عَلَى سَفِينَةٍ، فَأَصَابَ بَعْضُهُمْ أَعْلاَهَا وَبَعْضُهُمْ أَسْفَلَهَا، فَكَانَ الَّذِينَ فِي أَسْفَلِهَا إِذَا اسْتَقَوْا مِنَ المَاءِ مَرُّوا عَلَى مَنْ فَوْقَهُمْ، فَقَالُوا: لَوْ أَنَّا خَرَقْنَا فِي نَصِيبِنَا خَرْقًا وَلَمْ نُؤْذِ مَنْ فَوْقَنَا، فَإِنْ يَتْرُكُوهُمْ وَمَا أَرَادُوا هَلَكُوا جَمِيعًا، وَإِنْ أَخَذُوا عَلَى أَيْدِيهِمْ نَجَوْا، وَنَجَوْا جَمِيعًا».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 2493]
المزيــد ...
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"በአላህ ድንበር ላይ በአግባቡ የቆሙና የርሱን ድንበር የሚተላለፉ ሰዎች ምሳሌ በመርከብ ላይ (ቦታ ለመምረጥ) እጣ እንደተጣጣሉ ሰዎች ምሳሌ ነው። (በእጣው መሰረት) ከፊሉን የመርከቡ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉን ደግሞ የታችኛው ክፍል ደረሰው። የመርከቡ ታችኛው ክፍል ያሉት ውሃ ለመጠጣት የፈለጉ ጊዜ ላይኛው ክፍል ባሉት በኩል ያልፉ ነበርና "እኛም (ውሃ ለማግኘት) ፋንታችንን መርከቡን ብንሸነቁርና ከኛ በላይ ያሉትን ባናውካቸው መልካም ነው።" ተባባሉ። ከላይ ያሉት የታችኞቹ ፍላጎታቸውን እንዲፈፅሙ ከተዋቸው ሁሉም ይጠፋሉ። እጃቸውን ከያዙ ደግሞ እነሱም ይድናሉ። ሁሉም ይድናሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2493]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ ድንበር ላይ ለቆሙ፣ በአላህ ትእዛዝ ላይ ቀጥ ላሉ፣ በመልካም ለሚያዙና ከመጥፎ ለሚከለክሉ ሰዎች ምሳሌ አደረጉ። የአላህን ድንበር የሚተላለፉ፣ መልካምን የተዉና ውግዝን የሚተገብሩ ሰዎች በማህበረሰቡ መዳን ላይ የሚያሳድሩት አሻራ ምሳሌው በመርከብ እንደተሳፈሩ ሰዎች ምሳሌ ነው። የመርከቡ የላይኛው ክፍልና የታችኛው ክፍል የሚቀመጠውን ለመወሰን እጣ ተጣጣሉ። ከፊሉ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉ ደግሞ ታችኛው ክፍል ደረሰው። ከታች በኩል ያሉት ውሃ ማምጣት የፈለጉ ጊዜ ከላያቸው ወዳሉት ያልፉ ነበር። ከታች በኩል ያሉት "ባለንበት ስፍራ ከታች ብንቀደው ኖሮ በርሱ በኩል ውሃ እናገኝ ነበር። ከላያችን ያሉትንም አናስቸግርም ነበር።" አሉ። ከላይ በኩል ያሉት ይህንን እንዲፈፅሙ ከተዋቸው ሁሉንም እንደያዘች መርከቧ ትሰምጣለች። ከዚህ ተግባራቸው ለመከልከል ቆመው ማቀብ ከቻሉ ደሞ ሁለቱም ክፍሎች ባጠቃላይ ይድናሉ።