+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ مِنْ أَعْظَمِ الجِهَادِ كَلِمَةَ عَدْلٍ عِنْدَ سُلْطَانٍ جَائِرٍ».

[حسن لغيره] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 2174]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ትልቁ ጂሃድ የሚባለው ግፈኛ ባለስልጣን ዘንድ ፍትሀዊ ንግግርን መናገር ነው።"

[Hasan/Sound by virtue of corroborating evidence] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2174]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ከሚደረጉ የጂሃድ አይነቶች መካከል ጠቃሚውና ትልቁ እውነተኛና ፍትሀዊ ንግግርን ግፈኛና በደለኛ ባለስልጣን ወይም መሪ ዘንድ መናገር እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ትልቁን መገለጫ ነውና የሰራው። ይህም በንግግርም፣ በጽሑፍም፣ በተግባርም ይሁን ከዚህ ውጪ ባሉ ጥቅም የሚገኝበትና ጉዳት የሚወገድበት በሆነ በማንኛውም መልኩ ሊፈፀም ይችላል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الليتوانية الدرية الصربية الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ከጂሃድ አይነቶች እንደሆነ እንረዳለን።
  2. መሪን መምከር ከትላልቅ የጂሃድ አይነቶች አንዱ ነው። ነገር ግን በእውቀት፣ በጥበብና በማረጋገጥ መሆኑ ግዴታ ነው።
  3. ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: ይህ በላጩ ጂሃድ የሆነበትም ምክንያት ጠላትን የተዋጋ ሰው በተስፋና ስጋት መካከል ነው የሚሆነው። እንደሚያሸንፍም ሆነ እንደሚሸነፍ አያውቅም። የስልጣን ባለቤት ፊት ግን በእጁ የተሸነፍክ ሆነህ ነው የምትቀርበው፤ እርሱ ፊት እውነትን የተናገርክና በመልካም ያዘዝከው ጊዜ ራስህን ለጥፋት አጋርጠህና ነፍስህን ለሞት አዘጋጅተህ የምትቀርብ በመሆንህ ነው። ይህም ስጋቱ ያመዘነ ስለሆነ በላጩ የጂሀድ አይነት ሆነ። በላጩ ጂሀድ የሆነው መሪው ቃሉን ሰምቶ ቢቀበለው ጥቅሙ ለበርካታ ሰዎች ስለሚዳረስ በዚህም ጥቅም ስላለው ነው ያሉም አሉ።