+ -

عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«الْكَبَائِرُ: الْإِشْرَاكُ بِاللهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6675]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6675]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለትላልቅ ወንጀሎች አብራሩ። ትልቅ ወንጀል የሚባለውም ሰሪው በዱንያ ወይም በአኺራ ስለሚቀጣው ቅጣት ከባድ ዛቻ የተዛተበት ነው።
የመጀመሪያውም:- "በአላህ ማጋራት ነው።" ይህም ከአምልኮ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አምልኮ ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ፤ እንዲሁም ከአላህ ውጪ የሆነን አካል በተመላኪነቱ ፣ በጌትነቱ ወይም በስምና ባህሪያቱ አላህ በተለየበት ነገር ላይ ከአላህ ጋር እኩል ማድረግ ማለት ነው።
ሁለተኛው:- "የወላጆችን ሐቅ ማጓደል": ይህም ማንኛውም ወላጆችን ወደ ማወክ የሚዳርግ ንግግርም ይሁን ተግባር መፈፀምና ለነርሱ በጎ ማድረግን መተው ማለት ነው።
ሶስተኛው: "ነፍስን ያለ አግባብ ማጥፋት ነው።" ይህም በግፍ ወይም ወሰን በማለፍ መግደል ማለት ነው።
አራተኛው: "(የሚን አልገሙስ) አስማጭ መሀላ ነው።" ይህም እየዋሸ እንደሆነ እያወቀ በውሸት መማል ነው። በዚህም ስያሜ የተጠራቸው ሰውየውን ወንጀል ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ ስለምታሰምጠው ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የውሸት መሀላ አደገኝነቱና ወንጀልነቱ ከባድ ከመሆኑ አንፃር ተውበት እንጂ ምንም ማካካሻ የለውም።
  2. ሐዲሡ ውስጥ እነዚህ አራት ወንጀሎች ብቻ መጠቀሳቸው ወንጀልነታቸው ከባድ ስለሆነ እንጂ የቁጥር ገደብ አይደለም።
  3. ወንጀሎች ወደ ትላልቅና ትናንሽ ይከፈላሉ። ትላልቅ የሚባሉት: ማንኛውም አለማዊ ቅጣት የተቀመጠለት ወንጀል ለምሳሌ :- ቅጣቱ በሸሪዓዊ መቅጫ ህግ ውስጥ ያለ (ሑዱድ)፣ መረጋገም ያለበት፤ ወይም እሳት መግባትን የመሰለ አኺራዊ ዛቻ የመጣበት ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለያዩ ደረጃዎች አላቸው። የክልከላ ደረጃውም ከፊሉ ከከፊሉ ይከብዳል። ትናንሽ ወንጀሎች የሚባሉት ደግሞ ከትላልቅ ወንጀሎች ውጪ ያሉት ናቸው።