عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رضي الله عنهما أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِذَا دَخَلَ الرَّجُلُ بَيْتَهُ، فَذَكَرَ اللهَ عِنْدَ دُخُولِهِ وَعِنْدَ طَعَامِهِ، قَالَ الشَّيْطَانُ: لَا مَبِيتَ لَكُمْ، وَلَا عَشَاءَ، وَإِذَا دَخَلَ، فَلَمْ يَذْكُرِ اللهَ عِنْدَ دُخُولِهِ، قَالَ الشَّيْطَانُ: أَدْرَكْتُمُ الْمَبِيتَ، وَإِذَا لَمْ يَذْكُرِ اللهَ عِنْدَ طَعَامِهِ، قَالَ: أَدْرَكْتُمُ الْمَبِيتَ وَالْعَشَاءَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2018]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰማ:
"አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል። በሚገባ ወቅት አላህን ሳያወሳ የገባ እንደሁ ሰይጣን 'ማደሪያ አግኝታችኋል' ይላል። በሚበላበት ወቅትም አላህን ካላወሳ ደግሞ 'ማደሪያም እራትም አግኝታችኋል።' ይላል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2018]
ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤት በሚገባ ወቅትና ምግብ ከመመገባችን በፊት አላህን ማውሳት አዘዙ። እርሱ ቤት በሚገባ ወቅትና ምግቡን በሚጀምር ወቅት አላህን (ቢስሚላህ) በማለት ያወሳ ጊዜ ሰይጣን ለግብረ አበሮቹ "እዚህ ባለቤቱ አላህን በማውሳት ከናንተ የተጠበቀበት በሆነው ቤት ውስጥ ምንም ማደሪያም እራትም የላችሁም።" ይላቸዋል። ሰውዬው ቤቱ በሚገባ ወቅትና ምግብ በሚመገብበት ወቅት አላህን ካላወሳ ግን ሰይጣን ለግብረአበሮቹ እዚህ ቤት ውስጥ ማደሪያም እራትም እንዳገኙ ይናግራቸዋል።