عن أبي بَكرة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«إِذَا الْتَقَى الْمُسْلِمَانِ بِسَيْفَيْهِمَا فَالْقَاتِلُ وَالْمَقْتُولُ فِي النَّارِ»، فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ هَذَا الْقَاتِلُ، فَمَا بَالُ الْمَقْتُولِ؟ قَالَ: «إِنَّهُ كَانَ حَرِيصًا عَلَى قَتْلِ صَاحِبِهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 31]
المزيــد ...
ከአቢ በክረህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦
"ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው። " እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህ ገዳይ ሆኖ (እሳት መግባቱ መልካም) ተገዳዩ (እሳት የሚገባው) በምን ጥፋቱ ነው?" አልኩ። እርሳቸውም "እሱ ባልደረባውን ለመግደል ጉጉ ስለነበር ነው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 31]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁለት ሙስሊሞች እርስ በርሳቸው እያንዳንዳቸው የባልደረባውን ህይወት ማጥፋትን ቋምጠው በሰይፋቸው ሊጋደሉ የተገናኙ እንደሆነ ሁለቱም እሳት እንደሚገቡ ተናገሩ። ገዳዩ ባለደረባውን በመግደሉ ምክንያት እሳት ውስጥ ይገባል። ሰሐቦች የተገዳዩ እሳት መግባት ግራ አጋባቸው: እንዴት የእሳት ይሆናል? ብለው ጠየቁ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባልደረባውን ለመግደል በመጓጓቱ ፤ በገዳዩ ከመቀደም በስተቀር ከመግደል ምንም የከለከለው ነገር ስለሌለ እሱም ጭምር የእሳት መሆኑን ተናገሩ።