عَنْ أَبِي العَبَّاسِ سَهْلِ بْنِ سَعِدٍ السَّاعِدِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: جَاءَ رَجُلٌ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، دُلَّنِي عَلَى عَمَلٍ إِذَا عَمِلْتُهُ أَحَبَّنِي اللَّهُ وَأَحَبَّنِي النَّاسُ، فَقَالَ:
«ازْهَدْ فِي الدُّنْيَا يُحِبُّكَ اللَّهُ، وَازْهَدْ فِيمَا عِنْدَ النَّاسِ يُحِبُّكَ النَّاسُ».
[قال النووي: حديث حسن] - [رواه ابن ماجه وغيره بأسانيد حسنة] - [الأربعون النووية: 31]
المزيــد ...
ከአቡል ዓባስ ሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ብሰራው አላህም የሚወደኝ ሰዎችም የሚወዱኝ የሆነን ስራ ጠቁሙኝ!" እርሳቸውም:
"ከዱንያ ቸልተኛ ሁን አላህ ይወድሃል። ሰዎች ዘንድ ካለው ቸልተኛ ሁን ሰዎች ይወዱሃል።" አሉት።»
[قال النووي: حديث حسن] - [رواه ابن ماجه وغيره بأسانيد حسنة] - [الأربعون النووية - 31]
አንድ ሰውዬ ሲሰራው አላህም የሚወደው ሰዎችም የሚወዱት የሆነን ስራ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲጠቁሙት ጠየቀ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዱንያ ትርፍ የሆኑ እንደ አኺራም የማይጠቅሙ የሆኑ ነገሮችን በተውክና ዲንህ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉብህን ነገሮች የተውክ ጊዜ አላህ ይወድሃል። ሰዎች እጅ ያለን የዱንያ ጥቅም ችላ ያልክ ጊዜ ደሞ ሰዎች ይወዱሃል። ምክንያቱም ሰዎች በተፈጥሯቸው ንብረታቸውን ይወዷታልና በንብረታቸው የተጋፋቸውን ይጠሉታል። ንብረታቸውን የተወላቸውን ደግሞ ይወዱታል በማለት መለሱለት።