عَنِ النَّوَّاسِ بْنِ سِمْعَانَ الْأَنْصَارِيِّ رضي الله عنه قَالَ:
سَأَلْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الْبِرِّ وَالْإِثْمِ، فَقَالَ: «الْبِرُّ حُسْنُ الْخُلُقِ، وَالْإِثْمُ مَا حَاكَ فِي صَدْرِكَ، وَكَرِهْتَ أَنْ يَطَّلِعَ عَلَيْهِ النَّاسُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2553]
المزيــد ...
ከነዋስ ቢን ሰምዓን አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለበጎ ተግባርና ስለወንጀል ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም " በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2553]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለበጎ ተግባርና ስለወንጀል ተጠየቁ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ:
የበጎ ተግባር ትልቁ ነገር ከአላህ ጋር እርሱን በመፍራት፤ ከፍጡራን ጋር ደግሞ የሚያደርሱብንን አዛ (ችግር) በመቻል፣ ቁጣን በመቀነስ፣ ፊትን በመፍታት፣ ንግግርን በማሳመር፣ ዝምድናን በመቀጠል፣ በመታዘዝ፣ በመራራት፣ በጎ በመስራት፣ መልካም ቤተሰብና ባልደረባ በመሆን መልካም ስነምግባርን መላበስ ነው።
ወንጀል ማለት ደግሞ ልብህ ለርሱ ሳይከፈት ነፍስህ ውስጥ የተመላለሰ፣ የከነከነህ አሻሚ ነገር ነው። ስትሰራው ወንጀል ይሆን እያልክ ቀልብህ ውስጥ ጥርጣሬ የሚከሰትበትና የምትፈራው፣ ፀያፍ ስለሆነም አርአያ የሚሆኑ፣ ታላላቅና የተሟላ ስብዕና ያላቸው ሰዎች ፊት ጉዳዩ እንዲታወቅብህ የማትፈልገው ነው። ይህም ነፍስ በተፈጥሮዋ ሰዎች መልካም ስራዋን እንዲያውቁላት ነው የምትፈልገው። አንዳንድ ስራዋ መውጣቱን ከጠላች ግን ያ ስራ ወንጀል ነውና ምንም መልካም የለውም።