عن المِقدام بن معدي كرب رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«إِذَا أَحَبَّ الرَّجُلُ أَخَاهُ فَلْيُخْبِرْهُ أَنَّهُ يُحِبُّهُ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وأحمد] - [سنن أبي داود: 5124]
المزيــد ...

ከሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5124]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምእመናን መካከል መስተጋብራቸውን ከሚያጠናክሩና በመካከላቸውም ውዴታን ከሚያሰፍኑ ሰበቦች መካከል አንዱን ጠቀሱ። ይኸውም አንድ ሰው ወንድሙን የሚወደው ከሆነ እንደሚወደው ይንገረው አሉ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ለዓለማዊ ጥቅም ሳይሆን ጥርት ባለ መልኩ ለአላህ ብሎ መውደድ ያለውን ደረጃ እንረዳለን።
  2. መዋደዱና መግባባቱ እንዲጨምር ለአላህ ብለው የሚወዱትን እንደሚወዱት መንገር እንደሚበረታታ እንረዳለን።
  3. በምእመናን መካከል መዋደድ መስፋፋቱ ኢማናዊ የሆነውን ወንድማማችነት እንደሚያጠነክርና ማህበረሰቡንም ከመለያየትና ከመበታተን እንደሚታደግ እንረዳለን።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)