+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤمنينَ رضي الله عنها قَالَتْ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُعْجِبُهُ التَّيَمُّنُ، فِي تَنَعُّلِهِ، وَتَرَجُّلِهِ، وَطُهُورِهِ، وَفِي شَأْنِهِ كُلِّهِ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 168]
المزيــد ...

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦
«ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 168]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለማክበር የተገቡ የሆኑ ጉዳያቸውን ሲፈፅሙ በቀኝ መጀመርን ይወዱና ያስበልጡ ነበር። ከነዚህ ጉዳዮችም መካከል: ጫማ ሲያደርጉ በቀኝ እግር ይጀምራሉ፤ የጭንቅላታቸውን ፀጉርና ፂማቸውን ሲያበጥሩ፣ ሲቀቡና ሲያስውቡ በቀኝ ይጀምሩ ነበር፣ እጃቸውና እግራቸውን ዉዱእ ሲያደርጉም ቀኛቸውን ከግራ ያስቀድሙ ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية النيبالية الدرية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ኢማሙ ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፦ ይህ በሸሪዓ ውስጥ ቀጣይነት ያለው መርህ ነው። እርሱም ልብስና ሱሪ መልበስ፣ ጫማ መልበስ፣ መስጂድ መግባት፣ ጥርስን መፋቅ፣ መኳል፣ ጥፍርን መቁረጥ፣ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣ ፀጉር ማበጠር፣ የብብት ፀጉርን መንጨት፣ ጭንቅላትን መላጨት፣ ከሶላት ማሰላመት፣ የንፅህና አካላትን መታጠብ፣ ከሽንት ቤት መውጣት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መጨባበጥ፣ ጥቁሩን ድንጋይ ሰላም ማለትና የመሳሰሉትን በዚሁ ደረጃ ላይ ያሉ ክብርና ልቅና ያለውን ነገር በቀኝ መጀመር ይወደዳል። በተቃራኒው የሆነ ነገር ደግሞ ሽንት ቤት መግባት፣ ከመስጂድ መውጣት፣ መናፈጥ፣ ኢስቲንጃእ፣ ልብስና ሱሪ ማውለቅ፣ ጫማ ማውለቅና የመሳሰሉትን በግራ መጀመር ይወደዳል። ይህ ሁሉም ቀኝ ክብርና ልቅና ስላላት ነው።
  2. "ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።" የሚለው: ድርጊቶችን በቀኝ እጅ፣ በቀኝ እግር ፣ በቀኝ ጎን፣ መጀመርንና ነገሮችን በቀኝ መቀባበልን ያካትታል።
  3. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ከዉዱእ አካላት መካከል ቀኝን ማስቀደም የማይወደድበት አካላቶች አሉ። እነርሱም ሁለቱ ጆሮዎች፣ ሁለቱ መዳፎችና ጉንጮች ሲሆኑ እነዚህ ሁሉ እኩል ነው የሚፀዱት። ይህንን ማድረግ የማይችል አካሉ የተቆረጠና መሰል (አንድ ላይ ማድረግ የማይችል) አይነት ከሆነ ቀኝን ያስቀድማል።»