عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه:
أَنَّ نَفَرًا مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَأَلُوا أَزْوَاجَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنْ عَمَلِهِ فِي السِّرِّ؟ فَقَالَ بَعْضُهُمْ: لَا أَتَزَوَّجُ النِّسَاءَ، وَقَالَ بَعْضُهُمْ: لَا آكُلُ اللَّحْمَ، وَقَالَ بَعْضُهُمْ: لَا أَنَامُ عَلَى فِرَاشٍ، فَحَمِدَ اللهَ وَأَثْنَى عَلَيْهِ، فَقَالَ: «مَا بَالُ أَقْوَامٍ قَالُوا كَذَا وَكَذَا؟ لَكِنِّي أُصَلِّي وَأَنَامُ، وَأَصُومُ وَأُفْطِرُ، وَأَتَزَوَّجُ النِّسَاءَ، فَمَنْ رَغِبَ عَنْ سُنَّتِي فَلَيْسَ مِنِّي».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1401]
المزيــد ...
ከአነስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«የተወሰኑ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሚስቶች ስለርሳቸው ድብቅ (ቤት ውስጥ የሚሰሩት) ዒባዳ ጠየቁ። (የርሳቸውን የቤት ውስጥ ስራ ከሰሙ በኋላ) አንዱ እንዲህ አለ "እኔ ሴት አላገባም!" አንዱ ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም!" አለ። እርሳቸውም አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1401]
የተወሰኑ ሶሐቦች - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቤት ውስጥ በድብቅ ስለሚሰሩት ዒባዳ ለመጠየቅ ወደ ሚስቶቻቸው ቤት መጡ። የርሳቸው የቤት ውስጥ አምልኮ ሲነገራቸውም የራሳቸውን ስራ አሳንሰው ተመለከቱና እንዲህ አሉ: "እኛ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንፃር የት ነን? ለርሳቸው ያሳለፉትንም ሆነ የሚመጣውን ወንጀል ተምረዋል። እኛስ ከርሳቸው ተቃራኒ ምህረት ማግኘታችንን እንኳ አላወቅንም። ስለዚህ ይህን የአላህ ምህረት ለማግኘት አምልኳችን ከገደብ ያለፈ መሆን አለበት።" ቀጥለውም አንዱ "እኔ ሴት አላገባም!" አለ። ሁለተኛው ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም።" አለ። ይህ ንግግራቸውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ ደረሰና ተቆጡ። ለሰዎችም ኹጥባ አደረጉ። አላህን አመስግነው ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምንድነው ጉዳያቸው? ወላሂ እኔ ከሁላቹም እጅግ አላህን ፈሪውና ተጠንቃቂው ነኝ። ነገር ግን እኔ ሌሊት ለመቆም እንድበራታ እተኛለሁ፤ ለጾም እንድበራታም አፈጥራለሁ፤ ሴትንም አገባለሁ። ከኔ መንገድ አፈንግጦ ከኔ መንገድ ውጪ የተሟላ መንገድ እንዳለ የተመለከተና ከኔ መንገድ ውጪ የያዘ ሰው ከኔ አይደለም።"