عَنْ أَبِي بَكْرٍ الصِّدِّيقَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
نَظَرْتُ إِلَى أَقْدَامِ الْمُشْرِكِينَ عَلَى رُءُوسِنَا وَنَحْنُ فِي الْغَارِ، فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ لَوْ أَنَّ أَحَدَهُمْ نَظَرَ إِلَى قَدَمَيْهِ أَبْصَرَنَا تَحْتَ قَدَمَيْهِ، فَقَالَ: «يَا أَبَا بَكْرٍ، مَا ظَنُّكَ بِاثْنَيْنِ اللهُ ثَالِثُهُمَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2381]
المزيــد ...
ከአቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«እኛ ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን የአጋርያን እግር ከጭንቅላታችን በላይ ሆኖ ተመለከትኩት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ: ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመለከተን ነበር።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2381]
የአማኞች መሪ አቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በስደት ወቅት ስለነበረው ሁኔታ ሲተርኩ እንዲህ አሉ: እኛ የሠውር ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን ከጭንቅላታችን በላይ የአጋርያን እግር ሆኖ ተመለከትኩ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመከተናል።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ በእርዳታው፣ በእገዛውና በጥበቃው ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉት።