عَنْ مُعَاذَةَ قَالَتْ:
سَأَلْتُ عَائِشَةَ، فَقُلْتُ: مَا بَالُ الْحَائِضِ تَقْضِي الصَّوْمَ، وَلَا تَقْضِي الصَّلَاةَ؟ فَقَالَتْ: أَحَرُورِيَّةٌ أَنْتِ؟ قُلْتُ: لَسْتُ بِحَرُورِيَّةٍ، وَلَكِنِّي أَسْأَلُ. قَالَتْ: كَانَ يُصِيبُنَا ذَلِكَ، فَنُؤْمَرُ بِقَضَاءِ الصَّوْمِ، وَلَا نُؤْمَرُ بِقَضَاءِ الصَّلَاةِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 335]
المزيــد ...
ከሙዓዘህ እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«ዓኢሻን እንዲህ በማለት ጠየቅኳት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?" እርሷም "አንቺ ሐሩሪያ ነሽን?" አለችኝ። እኔም "ሐሩሪያ አይደለሁም። እንዲሁ እየጠየቅኩ ነው።" አልኳት። እርሷም "ይህ ጉዳይ ያጋጥመን ነበር። ፆምን ቀዷ በማውጣት (በማካካስ) ስንታዘዝ ሶላትን ቀዷ በማውጣት ግን አንታዘዝም ነበር።" አለች።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 335]
ሙዓዘተል ዓደዊያህ የአማኞች እናት የሆነችውን ዓኢሻን አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ በማለት ጠየቀቻት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?" እርሷም "አንቺ ለማጥበቅና ለማክበድ ጥያቄን የሚያበዙት ከሆኑት ከኸዋሪጆች ከሐሩሪያዎች ነሽን?" አለቻት። እኔም "ሐሩሪያ አይደለሁም። እንዲሁ እየጠየቅኩ ነው።" አልኳት። እርሷም "ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ሳለን የወር አበባ ያጋጥመን ነበር። ፆምን ቀዷ በማውጣት ስንታዘዝ ሶላትን ቀዷ በማውጣት ግን አንታዘዝም ነበር።" አለች።