عَنْ عَمَّارِ بنِ ياسِرٍ رضي الله عنه قال:
بَعَثَنِي رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي حَاجَةٍ، فَأَجْنَبْتُ فَلَمْ أَجِدِ الْمَاءَ، فَتَمَرَّغْتُ فِي الصَّعِيدِ كَمَا تَمَرَّغُ الدَّابَّةُ ثُمَّ أَتَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَذَكَرْتُ ذَلِكَ لَهُ فَقَالَ: «إِنَّمَا كَانَ يَكْفِيكَ أَنْ تَقُولَ بِيَدَيْكَ هَكَذَا» ثُمَّ ضَرَبَ بِيَدَيْهِ الْأَرْضَ ضَرْبَةً وَاحِدَةً، ثُمَّ مَسَحَ الشِّمَالَ عَلَى الْيَمِينِ، وَظَاهِرَ كَفَّيْهِ وَوَجْهَهُ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 368]
المزيــد ...
ከዓማር ቢን ያሲር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለአንድ ጉዳይ ላኩኝና የዘር ፈሳሽ ወጣኝ። ውሃ አላገኘሁምና እንስሳ መሬት ላይ እንደምትንከባለለው ተንከባለልኩኝ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣሁና ይህን ድርጊቴ አወሳሁላቸው። እርሳቸውም 'በእጅህ እንዲህ ብታደርግ በቂህ ነበር።' አሉና ከዚያም በሁለት እጃቸው መሬቱን አንድ ጊዜ መቱ። ከዚያም በግራ እጃቸው ቀኝ እጃቸውን አበሱ። የላይኛውን የመዳፋቸው ክፍልንና ፊታቸውን አበሱ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 368]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዓማር ቢን ያሲርን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለሆነ ጉዳይ ጉዞ ላኩት። በግንኙነት ወይም በተኛበት በስሜት የዘር ፈሳሽ በመውጣቱ ምክንያት ጀናባ አገኘው። የሚታጠብበት ውሃም አላገኘም። የሚያውቀው ዉዱእ ሲያጠፋ ለትንሹ ሐደሥ የሚደረገውን የተየሙም ብይን እንጂ፤ ጀናባ ሲያጋጥም የሚደረገውን የተየሙም ብይን አያውቅም ነበር። ስለ አፈፃፀሙ ከተመራመረ በኋላ ዉዹእ ሲጠፋ የምድር ገፅ ላይ በሚገኝ አፈር ከፊል የዉዱእ አካላትን እንደሚታበሰው ለጀናባ የሚደረገው የተየሙም አፈፃፀም ደግሞ የግድ መላ ሰውነትን በአፈር ማዳረስ መሆን አለበት ብሎ አሰበ። ይህም በውሃ ቀይሶት ነው። ሰውነቱን ባጠቃላይ እንዲነካም አፈር ላይ ተንከባለለና ሰገደ። ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመጣ ጊዜም ትክክል ነው የፈፀምኩት ወይስ አይደለም? የሚለውን ለማወቅ ያደረገውን አወሳላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁለቱም ሐደሦች ማለት እንደሽንት ካለው ዉዱእ የሚያጠፋው ትንሹ ሐደሥ እና እንደቭጀናባ ካለው ገላ የሚያስታጥበው ትልቁ ሐደሥ የአፀዳድ አፈፃፀምን ገለፁለት። እርሱም በሁለት እጆቹ አንድ ጊዜ አፈርን በመምታት ከዚያም በግራ እጁ ቀኝ እጁን ያብሳል፤ የመዳፎቹን የላይኛውን ክፍልና ፊቱን ያብሳል።