عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«قَارِبُوا وَسَدِّدُوا، وَاعْلَمُوا أَنَّهُ لَنْ يَنْجُوَ أَحَدٌ مِنْكُمْ بِعَمَلِهِ» قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ وَلَا أَنْتَ؟ قَالَ: «وَلَا أَنَا، إِلَّا أَنْ يَتَغَمَّدَنِيَ اللهُ بِرَحْمَةٍ مِنْهُ وَفَضْلٍ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2816]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ትክክለኛውን አካሄድ ተከተሉ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2816]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦች እንዲሰሩ፤ ወሰን ሳያልፉና ሳያጓድሉ በቻሉት ልክ አላህንም እንዲፈሩ፤ ስራቸው ተቀባይነት አግኝቶ በነርሱ ላይ የአላህ እዝነት እንዲወርድ ሰበብ እንዲሆንም በስራቸው ለአላህ በማጥራትና ሱናን በመከተል በትክክል መስራትን እንዲያስቡ አነሳሱ።
ቀጥለውም ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው ብቻ አይድንም። ይልቁንም የግድ የአላህ እዝነት ያስፈልገዋል ብለው ነገሯቸው።
ሰሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእርሶ ሥራ እንዲህ መጠኑ ከመግዘፉ ጋርም (መልካም ስራዎ ብቻውን) አያድኖትምን?" አሉ።
እርሳቸውም "እኔም ብሆን አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እስካልሸፈነኝ ድረስ በስራዬ ብቻ አልድንም።" አሉ።