+ -

عَنْ أَبِي بَكْرٍ الصِّدِّيقِ رضي الله عنه أَنَّهُ قَالَ: أَيُّهَا النَّاسُ، إِنَّكُمْ تَقْرَؤُونَ هَذِهِ الآيَةَ: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا عَلَيْكُمْ أَنْفُسَكُمْ لاَ يَضُرُّكُمْ مَنْ ضَلَّ إِذَا اهْتَدَيْتُمْ}، وَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِنَّ النَّاسَ إِذَا رَأَوْا الظَّالِمَ فَلَمْ يَأْخُذُوا عَلَى يَدَيْهِ أَوْشَكَ أَنْ يَعُمَّهُمُ اللَّهُ بِعِقَابٍ مِنْهُ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 2168]
المزيــد ...

ከአቡበከር አስሲዲቅ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እናንተ ሰዎች ሆይ! {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ! (ጠብቁ)። በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም።} የሚለውን አንቀፅ ታነቡታላችሁ። እኔ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ ከርሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2168]

ትንታኔ

አቡበከር አስሲዲቅ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሰዎች ይህቺን አንቀፅ እንደሚያነቡ ተናገሩ:
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ! (ጠብቁ)። በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም።} [አልማኢዳህ: 105]
ከዚህም አንቀፅ የሰው ልጅ ያለበት ግዴታ ነፍሱን በማስተካከል ላይ መልፋት ብቻ እንደሆነ፤ ነፍሱን ካስተካከለም የጠመመ ቢጠም ምንም እንደማይጎዳቸው፣ በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ዙሪያ እንደማይጠየቁ ይረዳሉ።
ይህ ግን (እነሱ እንዳሰቡት) አለመሆኑን ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው በመንገር አሳወቃቸው: ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው በመከልከል ላይ አቅሙ እያላቸው ከግፉ ካልከለከሉት አላህ መጥፎውን የሰራውንም ሆነ አይቶ ዝም ያለውን ሁሉንም እርሱ ዘንድ ባለ ቅጣት ሊጠቀልላቸው ይቀርባል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሙስሊሞች ግዴታ መመካከር፣ ወደ መልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነው።
  2. የአላህ አጠቃላይ ቅጣት ግፈኛን በግፉ ሲያካትተው መጥፎን እያየ በዚህ መጥፎ ነገር ላይ ማውገዝ እየቻለ ዝም ያለንም ያካትታል።
  3. ለአጠቃላዩ ማህበረሰብ ቁርአናዊ አንቀጾችን በትክክለኛው መንገድ ማስተማርና ማስገንዘብ እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. አላህ ባልገለፀው መልኩ መገንዘብ ውስጥ እንዳይወድቅ የአላህን መጽሐፍ ለመገንዘብ ትኩረት መስጠት በሁሉም የሰው ልጅ ላይ ግዴታ ነው።
  5. መመራት በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ከመተው ጋር አይረጋገጥም።
  6. የአንቀፁ ትክክለኛ ትርጉም: ነፍሳችሁን ከወንጀል በመጠበቅ ላይ ያዙ! ነፍሳችሁን ከጠበቃችሁ በኋላ ከመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ሲሳናችሁ ክልክሎቹን እስካልተዳፈራችሁ ድረስ የጠመመ ሰው በመዳፈሩ ምንም አይጎዳችሁም።