عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ:
«لَا يَمْنَعَنَّ رَجُلًا مِنْكُمْ مَخَافَةُ النَّاسِ أَنْ يَتَكَلَّمَ بِالْحَقِّ إِذَا رَآهُ أَوْ عَلِمَهُ».
[صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه وأحمد] - [مسند أحمد: 11403]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"ከናንተ መካከል እውነታን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገር ማናችሁንም ቢሆን ለሰዎች ያለው ፍራቻ እንዳይከለክለው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 11403]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በባልደረቦቻቸው መካከል ኹጥባ አደረጉ። ከመከሯቸው ጉዳዮችም አንዱ የትኛውም ሙስሊም እውነትን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገርና በርሱ ከማዘዝ ሰዎችንና ሀይላቸውን መፍራትና መስጋት እንዳይከለክለው ነው።