عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«قَالَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ: يُؤْذِينِي ابْنُ آدَمَ يَسُبُّ الدَّهْرَ وَأَنَا الدَّهْرُ، بِيَدِي الأَمْرُ أُقَلِّبُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4826]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህ አለ: ‹የአደም ልጅ ዘመንን በመሳደብ ያውከኛል። ዘመን እኔው ነኝ ፤ ነገሮች በኔ እጅ ናቸው፤ ምሽቱንና ቀኑን የምገለባብጠው እኔ ነኝ።›"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4826]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ በሐዲሠል ቁድሲይ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ። "የሰው ልጅ መከራና ችግር በሚወርዱበት ወቅት ጊዜን በማውገዝና በመሳደብ እኔን ያውከኛል ክብሬን ያሳንሳል። ምክንያቱም የሚከሰቱትን ነገሮች አስተናባሪው አላህ ሱብሓነሁ ብቻ ነው። ዘመንን መሳደብ አላህን ዐዘ ወጀል እንደመሳደብ ነው። ጊዜ ለአላህ ትእዛዝ የተገራ ፍጡር ነው። ክስተቶች በአላህ ትእዛዝ ይከሰታሉ።