عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ عُمَرَ رَضيَ اللهُ عنهُما قَالَ: مَرَرْنَا مَعَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى الْحِجْرِ، فَقَالَ لَنَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا تَدْخُلُوا مَسَاكِنَ الَّذِينَ ظَلَمُوا أَنْفُسَهُمْ، إِلَّا أَنْ تَكُونُوا بَاكِينَ؛ حَذَرًا أَنْ يُصِيبَكُمْ مِثْلُ مَا أَصَابَهُمْ» ثُمَّ زَجَرَ فَأَسْرَعَ حَتَّى خَلَّفَهَا.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2980]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር በሒጅር በኩል አለፍን። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለኛ እንዲህ አሉን:
"እነርሱን ያገኛቸው አምሳያ እንዳያገኛችሁ ያሰጋልና እያለቀሳችሁ ካልሆነ በቀር እነዚያ ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መኖሪያ እንዳትገቡ።" ከዚያም ግመላቸውን አንቀሳቀሱና አልፈዋት እስኪሄድ ድረስ በፍጥነት ተጓዙ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2980]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በሠሙዶች መኖሪያ በኩል ሲያልፉ ወደዚህ መንደር የሚገባ ሰው እነርሱ ላይ የደረሰውን በማስተንተን እያለቀሰ ካልሆነ በቀር ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መንደር ከመግባት ወይም ከመምጣት ከለከሉ። ይህም እነርሱን እንዳገኛቸው አይነት ቅጣት እንዳያገኘው ስለሚያሰጋ ነው። ቀጥለው እንስሳቸውን በጩኸት አስነስተው አልፈው እስኪሄዱ ድረስ ፈጥነው ተጓዙ።