عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنِينَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْها أَنَّهَا قَالَتْ:
أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِنَ الوَحْيِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلَّا جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ -وَهُوَ التَّعَبُّدُ- اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ العَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ، وَيَتَزَوَّدُ لِذَلِكَ، ثُمَّ يَرْجِعُ إِلَى خَدِيجَةَ فَيَتَزَوَّدُ لِمِثْلِهَا، حَتَّى جَاءَهُ الحَقُّ وَهُوَ فِي غَارِ حِرَاءٍ، فَجَاءَهُ المَلَكُ فَقَالَ: اقْرَأْ، قَالَ: «مَا أَنَا بِقَارِئٍ» قَالَ: «فَأَخَذَنِي فَغَطَّنِي حَتَّى بَلَغَ مِنِّي الجَهْدَ ثُمَّ أَرْسَلَنِي، فَقَالَ: اقْرَأْ، قُلْتُ: مَا أَنَا بِقَارِئٍ، فَأَخَذَنِي فَغَطَّنِي الثَّانِيَةَ حَتَّى بَلَغَ مِنِّي الجَهْدَ ثُمَّ أَرْسَلَنِي، فَقَالَ: اقْرَأْ، فَقُلْتُ: مَا أَنَا بِقَارِئٍ، فَأَخَذَنِي فَغَطَّنِي الثَّالِثَةَ ثُمَّ أَرْسَلَنِي، فَقَالَ: {اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ خَلَقَ الإِنْسَانَ مِنْ عَلَقٍ اقْرَأْ وَرَبُّكَ الأَكْرَمُ}»، [العلق:1-3] فَرَجَعَ بِهَا رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَرْجُفُ فُؤَادُهُ، فَدَخَلَ عَلَى خَدِيجَةَ بِنْتِ خُوَيْلِدٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، فَقَالَ: «زَمِّلُونِي، زَمِّلُونِي» فَزَمَّلُوهُ حَتَّى ذَهَبَ عَنْهُ الرَّوْعُ، فَقَالَ لِخَدِيجَةَ وَأَخْبَرَهَا الخَبَرَ: «لَقَدْ خَشِيتُ عَلَى نَفْسِي» فَقَالَتْ خَدِيجَةُ: كَلَّا وَاللَّهِ مَا يُخْزِيكَ اللَّهُ أَبَدًا، إِنَّكَ لَتَصِلُ الرَّحِمَ، وَتَحْمِلُ الكَلَّ، وَتَكْسِبُ المَعْدُومَ، وَتَقْرِي الضَّيْفَ، وَتُعِينُ عَلَى نَوَائِبِ الحَقِّ، فَانْطَلَقَتْ بِهِ خَدِيجَةُ حَتَّى أَتَتْ بِهِ وَرَقَةَ بْنَ نَوْفَلِ بْنِ أَسَدِ بْنِ عَبْدِ العُزَّى، ابْنَ عَمِّ خَدِيجَةَ، وَكَانَ امْرَأً تَنَصَّرَ فِي الجَاهِلِيَّةِ، وَكَانَ يَكْتُبُ الكِتَابَ العِبْرَانِيَّ، فَيَكْتُبُ مِنَ الإِنْجِيلِ بِالعِبْرَانِيَّةِ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَكْتُبَ، وَكَانَ شَيْخًا كَبِيرًا قَدْ عَمِيَ، فَقَالَتْ لَهُ خَدِيجَةُ: يَا ابْنَ عَمِّ، اسْمَعْ مِنَ ابْنِ أَخِيكَ، فَقَالَ لَهُ وَرَقَةُ: يَا ابْنَ أَخِي، مَاذَا تَرَى؟ فَأَخْبَرَهُ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خَبَرَ مَا رَأَى، فَقَالَ لَهُ وَرَقَةُ: هَذَا النَّامُوسُ الَّذِي نَزَّلَ اللَّهُ عَلَى مُوسَى، يَا لَيْتَنِي فِيهَا جَذَعًا، لَيْتَنِي أَكُونُ حَيًّا إِذْ يُخْرِجُكَ قَوْمُكَ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَوَ مُخْرِجِيَّ هُمْ؟»، قَالَ: نَعَمْ، لَمْ يَأْتِ رَجُلٌ قَطُّ بِمِثْلِ مَا جِئْتَ بِهِ إِلَّا عُودِيَ، وَإِنْ يُدْرِكْنِي يَوْمُكَ أَنْصُرْكَ نَصْرًا مُؤَزَّرًا. ثُمَّ لَمْ يَنْشَبْ وَرَقَةُ أَنْ تُوُفِّيَ، وَفَتَرَ الوَحْيُ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጀመሪያ ወሕይ ወደርሳቸው መውረድ የጀመረው በእንቅልፋቸው የሚያዩት መልካም ህልም ነበር። ንጋት ብርሃን (እንደተፍለቅላቂ ጎህ) በገሃዱ አለም የሚከሰት ቢሆን እንጂ አንድም ህልም አያዩም ነበር። ከዚያም ከሰዎች መገለል እርሳቸው ዘንድ ተወዳጅ ሆነ። በሒራ ዋሻም ከሰዎች ተገልለው ወደ ቤተሰባቸው ሳይመለሱ በርካታ ቀናቶችን አላህን እያመለኩ ያሳልፉ ነበር። ለዚህም ስንቅ ይዘው ነበር የሚወጡት። ከዛም ወደ ኸዲጃ ተመልሰው ለተመሳሳይ ድርጊት ስንቅ ይዘው ይወጡ ነበር። ይህንንም በሒራ ዋሻ ሳሉ እውነት ወደርሳቸው እስኪመጣ ድረስ ቀጠሉበት። መልአኩ ወደርሳቸው መጣና "አንብብ!" አላቸው። (ያኔ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልፁታል) እኔም "ማንበብ አልችልም!" አልኩት። እንዲህም አሉ "ጭንቅ እስኪለኝ ድረስ ይዞ ጨመቀኝና ለቀቀኝ።" አሁንም "አንብብ!" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። "አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ይዞኝ ጭንቅ እስኪለኝ ድረስ ጨመቀኝና ለቀቀኝ።" አሁንም "አንብብ!" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። "አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ይዞ ጭንቅ እስኪለኝ ድረስ ጨመቀኝና ለቀቀኝ።" መልአኩም እንዲህ አለኝ: {አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም) አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን} [አልዐለቅ: 1 - 3] የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እነዚህን አንቀጾች ሸምድደው ልባቸው እየተንቀጠቀጠ ተመለሱ። ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድም በመግባት "አከናንቡኝ! አከናንቡኝ!" አሉ። ድንጋጤው እስኪወገድላቸው ድረስም አከናነቧቸው። ለኸዲጃም ጉዳዩን ነገሯቸው። "ለነፍሴ ፈርቻለሁ።" አሉ። ኸዲጃም እንዲህ አለቻቸው "(እንደዚህ ከማሰብ) ተከልከል! በአላህ እምላለሁ! ከቶም አላህ አይተውህም። አንተ ዝምድና ትቀጥላለህ፤ ለደካሞች ትረዳለህ፤ ለተቸገሩ ትሰጣለህ፤ እንግዳ ታከብራለህ፤ እውነተኛ ጉዳዮች ላይ ትተባበራለህ።" እርሳቸውንም ይዛ የአጎቷ ልጅ ወደሆነው ወረቃ ቢን ነውፈል ቢን አሰድ ቢን ዐብዲል ዑዛ ዘንድ ሄደች። በጃሂሊያ ዘመን ክርስቲያን የሆነ ሰው ነበር። መጽሐፍን በዕብራይስጠኛ ይፅፍ ነበር። አላህ እንዲፅፍ የሻለትን ያህልም ኢንጂልን በዕብራይስጠኛ ይፅፍ ነበር። አይኑ የታወረ እጅግ የጃጀ ሽማግሌ ነበር። ኸዲጃም ለርሱ "የአጎቴ ልጅ ሆይ! እስኪ የወንድምህ ልጅ የሚለውን ስማ።" አለችው። ወረቃም ለርሳቸው "የወንድሜ ልጅ ሆይ! ምንድን ነው የምታየው?" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተመለከቱትን ነገሩት። ወረቃም ለርሳቸው "ይህ አላህ በሙሳ ላይ ያወረደው ናሙስ ነው። ህዝቦችህ ከሀገርህ በሚያስወጡህ ጊዜ ዋ ምኞቴ! ምነው ያኔ ጠንካራ ወጣት በሆንኩ! ዋ ምኞቴ በህይወት በኖርኩ!" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እነርሱ ያስወጡኛልን?" አሉ። እርሱም "አዎን አንተ ይዘኸው የመጣኸውን አምሳያ ይዞ የመጣ አንድም ሰው የለም ጠላት ተደርጎ የተያዘ ቢሆን እንጂ፤ የመልክተኝነት ዘመንህ ላይ ከደረስኩ ጠንካራ እርዳታን እረዳሀለሁ።" አላቸው። ከዚያም ግን ወረቃ ብዙም ሳይቆይ አረፈ። ወሕዩም ተቋረጠ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3]
የአማኞች እናት ዓኢሻ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንዲህ በማለት ስለ ወሕይ አጀማመር ተናገረች: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጀመሪያ ወሕይ ወደርሳቸው መውረድ የጀመረው በእንቅልፋቸው መልካም ህልም በማየት ነበር። በእንቅልፋቸው አንድም ህልም አያዩም ነበር እንደ ንጋት ብርሃን በሚመስል መልኩ በግልፅ የሚከሰት ቢሆን እንጂ። ቀጥሎ እርሳቸው ዘንድ ከሰዎች መገለል ተወዳጅ ሆነ። በሒራ ዋሻም ከሰዎች ተገልለው ወደ ቤተሰባቸው ሳይመለሱ በርካታ ቀናቶችን አላህን ሲያመልኩ ያሳልፉ ነበር። ለዚህም ስንቅ ይዘው ነበር የሚወጡት። ቀጥለው ወደ አማኞች እናት ኸዲጃ ረዲየሏሁ ዓንሃ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- በመመለስ ለተመሳሳይ ድርጊት ስንቅ ይዘው ይወጡ ነበር። ይህንን ማድረጋቸውንም በሒራ ዋሻ ሳሉ እውነት ወደርሳቸው እስኪመጣ ድረስ ቀጠሉበት። መልአኩ ጂብሪልም ዐለይሂ ሰላም ወደርሳቸው በመምጣት "አንብብ" አላቸው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ማንበብ አልችልም።" አሉ። እንዲህም አሉ: ጭንቅ ጥብብ እስኪለኝና እስኪሳነኝ ድረስ ጭምቅ አደረገኝ። ከዚያም ለቀቀኝና "አንብብ" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ጭንቅ ጥብብ እስኪለኝና እስኪሳነኝ ድረስ ጭምቅ አደረገኝ። ከዚያም ለቀቀኝና "አንብብ" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጭንቅ ጥብብ እስኪለኝና እስኪሳነኝ ድረስ ጭምቅ አደረገኝና እንዲህ አለኝ: {አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም* ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)* አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን} [አልዐለቅ: 1 - 3] ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንቀጾቹን ሸምድደው ሞትን ፈርተው ልባቸው እየተንቀጠቀጠ ተመለሱ። የአማኞች እናት ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ረዲየሏሁ ዓንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድም በመግባት እንዲህ አሉ: "በልብስ ጠቅልሉኝ! በልብስ ጠቅልሉኝ!" ፍርሃት እስኪለቃቸው ድረስም በልብስ ጠቀለሏቸው። ለኸዲጃም ጉዳዩን ነገሯትና እንዲህ አሉ: "ሞትን በነፍሴ ላይ ፈርቻለሁ።" ኸዲጃም እንዲህ አለች: "ይህንን ከመናገር ተከልከል! በአላህ እምላለሁ! አላህ በፍፁም አይተውህም። አንተ ዝምድናን ትቀጥላለህ፤ ራሱን ያልቻለን ደካማ ታግዛለህ፤ ሰዎች ካንተ ውጪ ማንም ዘንድ በማያገኙት መልኩ በመስጠት ምንም የሌለውን ድሃ ትረዳለህ፤ እንግዳን ታከብራለህ፤ ትክክለኛ ጉዳዮች ላይ ትተባበራለህ።" ኸዲጃም እርሳቸውን ይዛ የአጎቷ ልጅ ወደሆነው ወረቃ ቢን ነውፈል ቢን አሰድ ቢን ዐብዲል ዑዛ ዘንድ ሄደች። በጃሂሊያ ዘመን የጃሂሊዮችን እምነት በመተው ክርስቲያን የሆነ ሰው ነበር። አላህ እንዲፅፍ የሻለትን ያህልም ኢንጂልን በዕብራይስጠኛ ይፅፍ ነበር። አይኑ የታወረ እጅግ የጃጀ ሽማግሌ ነበር። ኸዲጃም ለርሱ እንዲህ አለች: "የአጎቴ ልጅ ሆይ! እስኪ የወንድምህ ልጅ የሚለውን ስማ።" ወረቃም ለርሳቸው "የወንድሜ ልጅ ሆይ! ምንድን ነው የምታየው?" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተመለከቱትን ነገሩት። ወረቃም ለርሳቸው "ይህ አላህ በሙሳ ላይ ያወረደው ጂብሪል ነው። ህዝቦችህ ከሀገርህ በሚያስወጡህ ጊዜ ዋ ምኞቴ! ጠንካራ ወጣት በሆንኩ! ዋ ምኞቴ በህይወትም በኖርኩ!" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እነርሱ ያስወጡኛልን?" አሉ። እርሱም "አዎን አንተ ይዘኸው የመጣኸውን አምሳያ ይዞ የመጣ አንድም ሰው የለም ጠላት ተደርጎ የተያዘና ጉዳት የደረሰበት ቢሆን እንጂ፤ የመልክተኝነት ዘመንህ ላይ ከደረስኩ ጠንካራ እርዳታን እረዳሀለሁ።" አላቸው። ከዚያም ግን ወረቃ ብዙም ሳይቆይ አረፈ። ወሕዩም ለተወሰነ ጊዜ ዘገየ።