عَنِ ‌ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا قَالَ:
أُنْزِلَ عَلَى رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَهُوَ ابْنُ أَرْبَعِينَ، فَمَكَثَ بِمَكَّةَ ثَلَاثَ عَشْرَةَ سَنَةً، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ، فَهَاجَرَ إِلَى الْمَدِينَةِ، فَمَكَثَ بِهَا عَشْرَ سِنِينَ، ثُمَّ تُوُفِّيَ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ.

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦
ቁርኣን የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አርባ ዓመታቸው ላይ ሳሉ ወረደ። በመካ አስራ ሦስት ዓመታት ቆዩ። ከዚያም በስደት ታዘዙ። ወደ መዲና ተሰደውም አስር ዓመታትን ቆዩ። ከዚያም ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አረፉ።

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) በአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ የወረደውና የተላኩበት ዕድሜ አርባ መሆኑን፤ ከወሕይ መውረድ በኋላም በመካ አስራ ሶስት አመት መቆየታቸውን፤ ከዚያም ወደ መዲና እንዲሰደዱ እንደታዘዙና በመዲናም አስር አመታት እንደቆዩ፤ ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በስልሳ ሶስት አመታቸው እንዳረፉ ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰሓቦች ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ታሪክ ትኩረት መስጠታቸውን እንረዳለን።
ተጨማሪ