عَنْ النَّوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ الْأَنْصَارِيِّ رضي الله عنه عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«ضَرَبَ اللهُ مَثَلًا صِرَاطًا مُسْتَقِيمًا، وَعَلَى جَنْبَتَيْ الصِّرَاطِ سُورَانِ، فِيهِمَا أَبْوَابٌ مُفَتَّحَةٌ، وَعَلَى الْأَبْوَابِ سُتُورٌ مُرْخَاةٌ، وَعَلَى بَابِ الصِّرَاطِ دَاعٍ يَقُولُ: أَيُّهَا النَّاسُ، ادْخُلُوا الصِّرَاطَ جَمِيعًا، وَلَا تَتَعَرَّجُوا، وَدَاعٍ يَدْعُو مِنْ فَوْقِ الصِّرَاطِ، فَإِذَا أَرَادَ يَفْتَحُ شَيْئًا مِنْ تِلْكَ الْأَبْوَابِ، قَالَ: وَيْحَكَ لَا تَفْتَحْهُ، فَإِنَّكَ إِنْ تَفْتَحْهُ تَلِجْهُ، وَالصِّرَاطُ الْإِسْلَامُ، وَالسُّورَانِ: حُدُودُ اللهِ، وَالْأَبْوَابُ الْمُفَتَّحَةُ: مَحَارِمُ اللهِ، وَذَلِكَ الدَّاعِي عَلَى رَأْسِ الصِّرَاطِ: كِتَابُ اللهِ، وَالدَّاعِي مِنِ فَوْقَ الصِّرَاطِ: وَاعِظُ اللهِ فِي قَلْبِ كُلِّ مُسْلِمٍ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد]
المزيــد ...

ከነዋስ ቢን ሰምዓን አል'አንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ የቀጥተኛውን መንገድ ምሳሌ አደረገ። በቀጥተኛው መንገድ ዳርና ዳር ሁለት አጥር (ግድግዳ) አሉ፤ አጥሮቹ ዘንድ የተከፈቱ በሮች ይገኛሉ፤ በሮቹ ላይም የተለቀቁ መጋረጃዎች አሉ፤ በመንገዱ በር ላይ "ሰዎች ሆይ! ሁላቹም ወደቀጥተኛው መንገድ ግቡ እንዳትጣመሙ!" የሚል ተጣሪ አለ። ከቀጥተኛው መንገድ ከላይ ሆኖ የሚለፍፍ አንድ ተጣሪ አለ ፤ ከነዛ በሮች አንዱን መክፈት የፈለገ ጊዜ "ወዮልህ እንዳትከፍተው! ከከፈትከው ትገባለህ!" ይለዋል። ቀጥተኛው መንገድ ኢስላም ነው፤ ሁለቱ አጥሮች የአላህ ድንበሮች ናቸው፤ የተከፈቱት በሮች የአላህ ክልከላዎች ናቸው፤ ከቀጥተኛው መንገድ አናት ላይ የሚጣራው የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከቀጥተኛው መንገድ ከላይ ሆኖ የሚጣራው በሁሉም ሙስሊም ቀልብ ውስጥ የሚገኝ የአላህ መካሪ ነው።"

Sahih/Authentic. - [At-Tirmidhi]

ትንታኔ

አላህ ኢስላምን ምንም ሳይጣመም በተዘረጋ ቀጥተኛ መንገድ መሰለው፤ በዚህ መንገድ ዳርና ዳር ሁለት ዙሪያውን የከበቡት አጥሮች አሉ እነሱም የአላህ ድንበሮች ናቸው፤ እነዚህ ሁለት አጥሮች የተከፈቱ በሮች ሲኖራቸው እነሱም የአላህ ክልከላዎች ናቸው፤ በመንገዱ የሚያልፍ ሰው በበሩ ውስጥ የሚገኘው ግልፅ እንዳይሆንለት በነዚህ በሮች ላይ የተዘጋጀ መጋረጃ አለ፤ በመንገዱ መነሻ ሰዎችን "መንገዳችሁን ወደጎንና ጎን ሳትዘነበሉ ቀጥ ብላችሁ ሂዱ!" እያለ የሚጠቁምና የሚመራ ተጣሪ አለ። ይህ ተጣሪም የአላህ መጽሐፍ ነው፤ እዚህ ቦታ ላይ የመንገዱ አናት ላይ ሆኖ የሚጣራ ሌላ ተጣሪም አለ፤ ይህ ተጣሪ መንገደኛው እነዛን የበሮቹ መጋረጃ ትንሽ ለመክፈት ባሰበ ቁጥር "ወዮልህ እንዳትከፍተው! መጋረጃውን ከከፈትከው ነፍስህን ውስጡ እንዳትገባ መቆጣጠር ስለማትችል ትገባለህ!" እያለ የሚያስጠነቅቀው ነው። ይህ ተጣሪም በሁሉም ሙስሊም ቀልብ ውስጥ የሚገኝ የአላህ መካሪ ነው። በማለት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምሳሌውን ፍቺ አብራሩት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ኢስላም እውነተኛ ሃይማኖትና ወደ ጀነት የሚያደርሰን ቀጥተኛ መንገድ ነው።
  2. የአላህን ድንበሮች ሐላልና ሐራም ባደረጋቸው ጉዳዮች አጥብቆ መያዝ ግዴታ መሆኑና በነዚህ ላይ መዘናጋት ለጥፋት እንደሚዳርግ እንረዳለን።
  3. የታላቁን ቁርኣን ደረጃና እርሱን መተግበር መበረታታቱ፤ በውስጡ መመሪያ፣ ብርሃንና ስኬትን ይዟል።
  4. አላህ በአማኞች ቀልብ ውስጥ ጥፋት ላይ ከመውደቅ የሚከለክላቸውና የሚገስፃቸውን ማኖሩ በባሮቹ ላይ ያለውን እዝነት ያሳያል።
  5. አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ ወንጀል ውስጥ ከመውደቅ የሚከለክላቸው አስጠንቃቂዎች ማድረጉን ተረድተናል።
  6. ከማስተማር መንገዶች መካከል ትምህርቱ ግልፅና ለመረዳት ቅርብ እንዲሆን ምሳሌ መጥቀስ አንዱ እንደሆነ ተረድተናል።