عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رضي الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا تَعَلَّمُوا الْعِلْمَ لِتُبَاهُوا بِهِ الْعُلَمَاءَ، وَلَا لِتُمَارُوا بِهِ السُّفَهَاءَ، وَلَا تَخَيَّرُوا بِهِ الْمَجَالِسَ، فَمَنْ فَعَلَ ذَلِكَ، فَالنَّارُ النَّارُ».

[صحيح] - [رواه ابن ماجه] - [سنن ابن ماجه: 254]
المزيــد ...

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት፣ በመድረኮች ላይ ቅድሚያ እንድትመረጡበት በማለም እንዳትቀስሙ። ይህን የፈፀመ (ለርሱ) እሳት አለው እሳት አለው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 254]

ማብራሪያ

ዑለሞችን ለመወዳደርና ለመፎካከር፣ እኔ እንደናንተው ዓሊም ነኝ የሚለውን ለማሳየት ወይም ቂሎችንና ደካማ ግንዛቤ ያላቸውን ልትሟገቱና ልታናግሩ ወይም በመድረኮች ግንባር ቀደም ለመሆንና ከሌላው ቅድሚያ እንዲሰጠው በማለም ዕውቀት ከመፈለግ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስጠነቀቁ። ይህን የፈፀመ ሰው፤ ለአላህ ብሎ ዕውቀት በመፈለግ ላይ እሱ ለይዩልኝና ያለ ኢኽላስ በመስራቱ እሳት ይገባዋል።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ዕውቀትን ሊፎካከርበት ወይም ሊሟገትበት ወይም በመድረኮች ቅድሚያ እንዲሰጠውና ለመሳሰሉት አላማዎች የተማረ ሰው በእሳት እንደተዛተበት እንረዳለን።
  2. ዕውቀትን ለሚማርና ለሚያስተምር ሰው ኒያን ማጥራት አንገብጋቢ ነው።
  3. ኒያ የሥራ መሰረት መሆኑንና ምንዳም በኒያ ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ተረድተናል።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (68)