عَنْ ‌أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ قَالَ:
كَانَ أَهْلُ الْكِتَابِ يَقْرَؤُونَ التَّوْرَاةَ بِالْعِبْرَانِيَّةِ، وَيُفَسِّرُونَهَا بِالْعَرَبِيَّةِ لِأَهْلِ الْإِسْلَامِ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَا تُصَدِّقُوا أَهْلَ الْكِتَابِ وَلَا تُكَذِّبُوهُمْ، وَقُولُوا: {آمَنَّا بِاللهِ وَمَا أُنْزِلَ إِلَيْنَا} [البقرة: 136] الْآيَةَ».

[صحيح] - [رواه البخاري]
المزيــد ...

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦
"የመጽሐፉ ባለቤቶች ለሙስሊሞች ተውራትን በይብራይስጠኛ እያነበቡ ወደ ዐረብኛ ይተረጉሟት ነበር። የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ። [አልበቀራህ: 136]"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የመጽሐፍ ባለቤቶች ከመጽሐፎቻቸው በሚያወሩት ነገር ከመሸወድ ኡመታቸውን አስጠነቀቁ። ይህም በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዘመን አይሁዶች ተውራትን በይብራይስጠኛ ቋንቋ (የአይሁዶች ቋንቋ ነው) እያነበቡ ወደ ዐረብኛ ይተረጉሙት ነበር። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ "የመጽሐፍ ባለቤቶችን አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም" ይህ ግን እውነተኝነቱ ከውሸቱ ባልታወቀበት ጉዳይ ነው። ይህንንም ያሉበት አላህ ወደኛ በወረደው ቁርኣንና ወደነርሱ በወረደው መጽሐፍ እንድናምን ስላዘዘን ነው። ነገር ግን እነሱ ከነዚህ መጽሐፎቻቸው እያጣቀሱ የሚተርኩትን ጉዳዮች በሸሪዐችን እውነተኛውን ከውሸተኛው የሚገልፅልን ስላልተቀመጠ ጤነኛውን ከበሽተኛው ለይተን የምናውቅበት መንገድ የለም። ስለዚህ ፍርድ ከመስጠት እንታቀባለን። መጽሐፉን በመበረዛቸው ላይ እንዳንጋራቸው አናምናቸውም። አላህ እንድናምነው ያዘዘን የሆነን ትክክለኛ ነገር አውርተው ያወገዘ ሰው እንዳንሆንም አናስተባብላቸውም። ስለዚህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ እንድንል አዘዙን። {"በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሓቅም ወደ ያዕቆብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን" በሉ።} [አልበቀራህ: 136]

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የመጽሐፍ ባለቤቶች የተናገሯቸው ጉዳዮች ሶስት ክፍሎች ናቸው።
  2. አንዱ ክፍል: ቁርኣንና ሐዲሥን የሚገጥም የሆነ ነው ይህም እናምንበታለን። ሁለተኛው ክፍል: ቁርኣንና ሐዲሥን የሚቃረን ሲሆን ይህም ጥመትና የሚስተባበል ነው። ሦስተኛው ክፍል: በቁርኣንም ሆነ በሐዲሥ ውስጥ እውነተኝነቱንም ስህተቱንም የሚጠቁም አልተገለፀም። ይህ ይወራል ነገር ግን አይታመንበትምም አይስተባበልም።