عَنْ زِيَادِ بْنِ لَبِيدٍ رضي الله عنه قَالَ:
ذَكَرَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ شَيْئًا، فَقَالَ: «ذَاكَ عِنْدَ أَوَانِ ذَهَابِ الْعِلْمِ» قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَكَيْفَ يَذْهَبُ الْعِلْمُ، وَنَحْنُ نَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَنُقْرِئُهُ أَبْنَاءَنَا وَيُقْرِئُهُ أَبْنَاؤُنَا أَبْنَاءَهُمْ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ؟ قَالَ: «ثَكِلَتْكَ أُمُّكَ زِيَادُ، إِنْ كُنْتُ لَأُرَاكَ مِنْ أَفْقَهِ رَجُلٍ بِالْمَدِينَةِ، أَوَلَيْسَ هَذِهِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى يَقْرَؤونَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ، لَا يَعْمَلُونَ بِشَيْءٍ مِمَّا فِيهِمَا؟!».

[صحيح لغيره] - [رواه ابن ماجه]
المزيــد ...

ዚያድ ቢን ለቢድ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ቁርኣን እየቀራን ፣ ልጆቻችንን እያቀራን፣ ልጆቻችንም ልጆቻቸውን እስከ እለተ ትንሳኤ እያቀሩ እንዴት ዕውቀት ይጠፋል?" አልኳቸው። እሳቸውም "እናትህ ትጣህ! ዚያድ በመዲና ጥልቅ ግንዛቤ ያለህ አድርጌ አይህ ነበርኩ። እነዚህ አይሁድና ክርስቲያን ተውራትና ኢንጂልን እየቀሩ ውስጣቸው ያለውን ምንም የማይሠሩ አይደሉምን?!" አሉኝ።

Sahih/Authentic by virtue of corroborating evidence. - [Ibn Maajah]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በባልደረቦቻቸው መሀል ተቀምጠው ሳለ እንዲህ አሉ፦ "ይህ ወቅት እውቀት ከሰዎች የሚነጠቅና የሚነሳበት ወቅት ነው።" ይህኔ ዚያድ ቢን ለቢድ አልአንሷሪይ በመደነቅ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጠየቁ። እንዲህም አሉ፦ "ቁርኣንን ቀርተነዋል፣ በቃላችን ሸምድደነዋል በአላህ እምላለሁ! እንቀራዋለን፣ ሴቶቻችንንም ልጆቻችንንም፣ የልጅ ልጆቻችንንም እያስቀራነው እንዴት ዕውቀት ይነሳል ከኛ እንዴት ይጠፋል?!" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመደነቅ እንዲህ አሉ: "ዚያድ ሆይ! እናትህ ትጣህና ከመዲና ነዋሪዎች ውስጥ ከሚገኙ ዐሊሞች እቆጥርህ ነበርኩ።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሱ ዕውቀት የሚጠፋው ቁርኣን በመጥፋቱ እንዳልሆነ ነገር ግን ዕውቀት የሚጠፋው በዕውቀት መሥራት ሲጠፋ እንደሆነ አብራሩለት። ተውራትና ኢንጂል አይሁዶችና ክርስቲያኖች ዘንድ አለ። ከዚህም ጋር ምንም አልጠቀማቸውምም የታለመለትንም ግብ አላሳኩም። የታለመለት ዓላማ ባወቁት መሥራት ነበርና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቁርኣንና መጽሐፎች በሰዎች እጅ መኖራቸው ብቻ ካልተሰራባቸው በስተቀር ምንም አይፈይዱም።
  2. የዕውቀት መጥፋት በተለያየ መልኩ ይከሰታል። ከነሱም ውስጥ: - የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሞት፣ የዑለሞች ሞት፣ በዕውቀት መስራት መተው ይጠቀሳሉ።
  3. ከሰዓቲቱ ምልክቶች ውስጥ የዕውቀት መጥፋትና በሱ አለመስራት ይጠቀሳል።
  4. በዕውቀት መሥራት ላይ መነሳሳቱ እሱ ነውና ዋናው የተፈለገው።