+ -

عن أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ رضي الله عنه قال:
بينما نحن جلوس مع النبي صلى الله عليه وسلم في المسجد دخل رجل على جمل، فأناخه في المسجد ثم عقله، ثم قال لهم: أيكم محمد؟ والنبي صلى الله عليه وسلم متكئ بين ظهرانيهم، فقلنا: هذا الرجل الأبيض المتكئ. فقال له الرجل: يا ابن عبد المطلب فقال له النبي صلى الله عليه وسلم: «قد أجبتك». فقال الرجل للنبي صلى الله عليه وسلم: إني سائلك فمشدد عليك في المسألة، فلا تجد علي في نفسك؟ فقال: «سل عما بدا لك» فقال: أسألك بربك ورب من قبلك، آلله أرسلك إلى الناس كلهم؟ فقال: «اللهم نعم». قال: أنشدك بالله، آلله أمرك أن نصلي الصلوات الخمس في اليوم والليلة؟ قال: «اللهم نعم». قال: أنشدك بالله، آلله أمرك أن نصوم هذا الشهر من السنة؟ قال: «اللهم نعم». قال: أنشدك بالله، آلله أمرك أن تأخذ هذه الصدقة من أغنيائنا فتقسمها على فقرائنا؟ فقال النبي صلى الله عليه وسلم: «اللهم نعم». فقال الرجل: آمنت بما جئت به، وأنا رسول من ورائي من قومي، وأنا ضمام بن ثعلبة أخو بني سعد بن بكر.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 63]
المزيــد ...

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦
መስጂድ ውስጥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። መስጂድ ውስጥ ግመሉን ካንበረከከ በኋላ አሰራት። ከዚያም ለነሱ እንዲህ አላቸው፦ "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመካከላቸው ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው። ለሳቸውም እንዲህ አላቸው "የዐብዱል ሙጠሊብ ልጅ ሆይ!" ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "አቤት ብያለሁ" አሉት። ሰውዬውም ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አላቸው፦ "እኔ እጠይቆታለሁ ስጠይቆት ጠንከር አደርግቦታለሁና ውስጦ በኔ ቅር እንዳይሰኝ።" እሳቸውም፦ "የፈለግከውን ጠይቅ!" አሉት። እሱም፦ "በአንተና ከአንተ በፊት ለነበሩት ጌታ በሆነው እጠይቅሀለሁ! አላህ ነውን ወደ ሰዎች ባጠቃላይ የላከህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። እሱም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን በቀንና በምሽት አምስት ሶላቶች እንድንሰግድ ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ከአመት ይህንን ወር እንድንፆም ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም በመቀጠል "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ይህንን ምፅዋት ከሀብታሞቻችን ወስደህ ለድሀዎቻችን እንድታከፋፍል ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም "አዎን" አሉት። ሰውዬውም፦ "ይዘውት በመጡት አምኛለሁ፤ ከኋላዬ ካሉ ህዝቦቼ የተላኩኝ መልክተኛ ነኝ። እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 63]

ትንታኔ

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-፦ መስጂድ ውስጥ ሰሐቦች ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠው ሳለ ድንገት አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። ግመሉን ካንበረከከ በኋላም አሰራት። ከዚያም "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" በማለት ጠየቃቸው። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሰዎች መሀል ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው። ሰውዬውም ለርሳቸው፦ "የዐብዱል ሙጠሊብ ልጅ ሆይ!" አላቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለርሱ "ሰምቸሀለሁ ጠይቅ እመልስልሀለሁ።" አሉት። ሰውዬውም ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "እኔ እጠይቆታለሁ ስጠይቆት ጠንከር አደርግቦታለሁና ውስጦ በኔ ቅር እንዳይሰኝ።" አላቸው። ማለትም "በኔ እንዳይቆጡ በኔም መጨናነቅ እንዳያገኞት።" እሳቸውም፦ "የምትፈልገውን ጠይቅ" አሉት። እሱም "በእርሶና ከእርሶ በፊት ለነበሩት ጌታ በሆነው እጠይቆታለሁ! አላህ ነውን ወደ ሰዎች የላኮት?" አላቸው። እውነትነቱን ለማፅናት "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። ሰውዬውም፦ "በአላህ ስም እማፀኖታለሁ! አላህ ነውን በቀንና በምሽት አምስት ሶላቶች እንድንሰግድ ያዘዞት?" አላቸው። (ግዴታ ሶላቶችን) "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። "በአላህ ስም እማፀኖታለሁ! አላህ ነውን ከአመት ይህንን ወር እንድንፆም ያዘዘህ?" አላቸው። (ማለትም የረመዳንን ወር) "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ይህንን ምፅዋት ከሀብታሞቻችን ወስደህ ለድሀዎቻችን እንድታከፋፍል ያዘዘህ?" አላቸው። (ዘካ ለማለት ነው።) ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። ይህኔ ዺማም ሰለመ። ለነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ህዝቦቹን ወደ ኢስላም እንደሚጣራ ነገራቸው። ቀጥሎ ራሱን ከበኑ ሰዕድ ቢን በክር የሆነ ዺማም ቢን ሠዕለባህ እንደሆነ በመናገር አስተዋወቃቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መተናነስ፤ ሰውየው በርሳቸውና በባልደረቦቻቸው መካከል መለየት ተስኖት ነበር።
  2. የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰናይ ምግባር ፣ ለጠያቂው ለስለስ ብለው መመለሳቸው፣ መልካም አመላለስ ጥሪ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከሚያደርጉ ሰበቦች አንዱ መሆኑን፤
  3. ሰውን በንጣት፣ በቅላት፣ በርዝመት፣ በእጥረትና በመሳሰሉት ማነወር በማይታሰብበትና ሰውዬው በማይጠላው መገለጫው ማሳወቅ እንደሚፈቀድ፤
  4. ካፊር ለጉዳይ መስጂድ መግባት እንደሚፈቀድለት፤
  5. በሐዲሡ ውስጥ ሐጅ ያልተጠቀሰው ምናልባት ሰውዬው በመጣበት ወቅት ሐጅ ግዴታ ያልተደረገ ሆኖ ሊሆን ይችላል።
  6. በመስለሙ ብቻ ህዝቦቹን ለመጣራት መጓጓቱ ሰሐቦች ሰዎችን በመጣራት ላይ ያላቸውን ጉጉት ያስረዳናል።