عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«كُلُّ أُمَّتِي يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ إِلَّا مَنْ أَبَى»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، وَمَنْ يَأْبَى؟ قَالَ: «مَنْ أَطَاعَنِي دَخَلَ الْجَنَّةَ، وَمَنْ عَصَانِي فَقَدْ أَبَى».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 7280]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡
"ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን እምቢ ይላል?" አሉ። እሳቸውም "እኔን የታዘዘኝ ጀነት ገባ ፤ እኔን ያመፀኝ ደግሞ በርግጥም እምቢ ብሏል።" በማለት መለሱ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7280]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት ከመግባት ራሱን ያቀበ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ህዝባቸው ጀነት እንደሚገቡ ተናገሩ።
ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ራሱን ከጀነት ያቅባል?" አሉ።
እሳቸውም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም : "መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከተለና የታዘዘ ጀነት ገባ። ያመፀና ለሸሪዐ ታዛዥ ያልሆነ ሰው ግን በርግጥም በመጥፎ ስራዎቹ ጀነት ከመግባት ራሱን አቅቧል።" በማለት መለሱላቸው።