عن عبدِ الله بن عمرو رضي الله عنهما قال:
كنتُ أكتبُ كلَّ شيءٍ أسمعُه من رسولِ الله صلَّى الله عليه وسلم أُريدُ حفْظَه، فنهتْني قريشٌ، وقالوا: أتكْتبُ كلَّ شيءٍ تَسمَعُه من رسول الله صلَّى الله عليه وسلم، ورسولُ الله صلَّى الله عليه وسلم بَشَرٌ يتكلَّمُ في الغضَبِ والرِّضا؟ فأمسَكتُ عن الكتاب، فذكرتُ ذلك لرسول الله صلَّى الله عليه وسلم، فأومأ بإصبَعِه إلى فيه، فقال: «اكتُبْ، فوالذي نفسي بيدِه، ما يَخرُجُ منه إلا حقٌّ».
[صحيح] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 3646]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምሰማውን ነገር ሁሉ መጠበቅ ፈልጌ እፅፈው ነበር። ቁረይሾች እንዲህ በማለት ከለከሉኝ 'ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምትሰማውን ነገር ሁሉ ትፅፋለህን? የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኮ ሰው ናቸው በቁጣና በደስታ ሰአትም ይናገራሉ!' ከመፃፍ ተቆጥቤ ይህንን ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳሁ። እሳቸውም በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: ' ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 3646]
ዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: ሁሉንም ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምሰማውን ነገር በጽሑፍ መጠበቅ ፈልጌ እጽፈው ነበር። ከቁረይሽ የሆኑ ሰዎችም እንዲህ በማለት ከለከሉኝ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰው ናቸው በቁጣና በደስታ ሰአትም ይናገራሉ፤ ሊሳሳቱም ይችላሉ።" እኔም ከመጻፍ ተቆጠብኩኝ።
እነርሱ የተናገሩትን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገርኳቸው። በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: "ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በደስታም ይሁን በንዴት በማንኛውም ሁኔታ ላይ ብሆን ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።"
በርግጥ ከፍ ያለው አላህም ስለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብሏል፦ {ከልብ ወለድም አይናገርም።* እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጂ ሌላ አይደለም።} [አንነጅም:3 -4]