عن عَمْرُو بْنُ عَامِرٍ عَنْ ‌أَنَس بن مالك قَالَ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَوَضَّأُ عِنْدَ كُلِّ صَلَاةٍ، قُلْتُ: كَيْفَ كُنْتُمْ تَصْنَعُونَ؟ قَالَ: يُجْزِئُ أَحَدَنَا الْوُضُوءُ مَا لَمْ يُحْدِثْ.

[صحيح] - [رواه البخاري]
المزيــد ...

ዐምር ቢን ዓሚር ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር። 'እናንተስ እንዴት ነበር የምታደርጉት?' አልኩኝ። አነስም 'ዉዱእ እስካላጠፋን ድረስ (የነበረን) ዉዱእ ይበቃን ነበር።' አለ።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ ባያጠፉ ራሱ ለሁሉም ግዴታ ሶላቶች ዉዱእ ያደርጉ ነበር። ይህም ተጨማሪ ምንዳና ትሩፋትን ለማግኘት ነው።
ዉዱእ እስካለው ድረስ በአንድ ዉዱእ ከአንድ ግዴታ ሶላት በላይ መስገድም ይፈቀድለታል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አብዝተው ይሰሩት የነበረው የበለጠ ሙሉ የሆነውን በመፈለግ ለሁሉም ሶላት ዉዱእ ማድረግ ነው።
  2. ለሁሉም ሶላት ዉዱእ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  3. በአንድ ዉዱእ ከአንድ ሶላት በላይ መስገድ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።