عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ:
تَوَضَّأَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَرَّةً مَرَّةً.
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 157]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 157]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ አንድ ወቅቶች ዉዱእ ያደረጉ ጊዜ ሁሉንም የዉዱእ አካላቶቻቸው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ያጥቡ ነበር። ፊታቸውን ‐ መጉመጥመጥና ውሀውን ወደ አፍንጫ ውስጥ ስቦ መልሶ ማውጣትን ጨምሮ‐ ፣ ሁለት እጃቸውንና ሁለት እግራቸውን አንድ አንድ ጊዜ ያጥቡ ነበር። ይህም ዝቅተኛው የግዴታ መጠን ነው።