عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«لَا يَقْبَلُ اللهُ صَلَاةَ أَحَدِكُمْ إِذَا أَحْدَثَ حَتَّى يَتَوَضَّأَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6954]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6954]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ትክክለኝነት ከሚያስፈልጉ መስፈርቶች መካከል ጠሀራ አንዱ መሆኑን ገለፁ። ስለሆነም ሶላት መስገድ በፈለገ ሰው ላይ እንደሰገራ ወይም ሽንት ወይም እንቅልፍና መሰል ሌላ ዉዱእ ከሚያፈርሱ ነገሮች መካከል አንድም አፍራሽ ነገር ከተከሰተ ዉዱእ ማድረግ ግዴታው ነው።