عَنْ ‌عَبْدِ اللهِ بْنِ زَيْدٍ رضي الله عنه:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ تَوَضَّأَ مَرَّتَيْنِ مَرَّتَيْنِ.

[صحيح] - [رواه البخاري]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ አድርገዋል።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ወቅት ላይ ዉዱእ ያደረጉ ጊዜ ሁሉንም የዉዱእ አካላቶቻቸው ሁለት ሁለት ጊዜ ያጥቡ ነበር። ፊታቸውን ‐ መጉመጥመጥና ውሀውን ወደ አፍንጫ ውስጥ ስቦ መልሶ ማውጣትን ጨምሮ‐ ፣ ሁለት እጃቸውንና ሁለት እግራቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያጥቡ ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አካላቶቻችንን ስናጥብ ግዴታ ያለብን አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ከዚህ በላይ መጨመር ተወዳጅ ነው።
  2. አንድ አንድ ወቅት ላይ ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ ማድረግ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ጭንቅላትን በማበስ ዙሪያ የተደነገገው አንድ ጊዜ ብቻ ማበስ ነው።