عَنْ ‌أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا وَجَدَ أَحَدُكُمْ فِي بَطْنِهِ شَيْئًا، فَأَشْكَلَ عَلَيْهِ أَخَرَجَ مِنْهُ شَيْءٌ أَمْ لَا، فَلَا يَخْرُجَنَّ مِنَ الْمَسْجِدِ حَتَّى يَسْمَعَ صَوْتًا، أَوْ يَجِدَ رِيحًا».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ) ከመስጂድ አይውጣ።'"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ሰጋጅ ከሆዱ ውስጥ አንዳች ነገር መውጣት አለመውጣቱን አስመልክቶ ከተጠራጠረ የፈስ ድምፅ በመስማት ወይም ጠረን በማሽተት ዉዱእ የሚያጠፋ ነገር መከሰቱን እርግጠኛ እስኪሆን ድረስ ዉዱእ ለመድገም ብሎ ሶላቱን አቋርጦ አይውጣ። የተረጋገጠ ነገር በጥርጣሬ አይበላሽምና። እሱ ዉዱእ እንደነበረው እርግጠኛ ነው፤ ዉዱእ ማጥፋቱ ግን አጠራጣሪ ነገር ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ሐዲሥ ከኢስላም መሰረቶች አንዱና ከፊቅህ መርሆዎች መካከል አንዱ መርህ ነው። እርሱም: የተረጋገጠ ነገር በጥርጣሬ አይወገድም ነው። መሰረቱ ተቃራኒው እስኪረጋገጥ ድረስ ሁሉም ነገር በነበረበት መጽናቱ ነው።
  2. ጥርጣሬ በጠሀራ ላይ ተፅእኖ እንደማያሳድር እንረዳለን። አንድ ሰጋጅ ዉዱእ ማጥፋቱን እርግጠኛ እስካልሆነ ድረስ በዉዱኡ ላይ እንደፀና ይቆያል።