+ -

عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«لَا ضَرَرَ وَلَا ضِرَارَ، مَنْ ضَارَّ ضَرَّهُ اللَّهُ، وَمَنْ شَاقَّ شَقَّ اللَّهُ عَلَيْهِ».

[صحيح بشواهده] - [رواه الدارقطني] - [سنن الدارقطني: 3079]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።"

[በማመሳከሪያዎቹ ሶሒሕ ነው።] - [ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።] - [ሱነን ዳረቁጥኒይ - 3079]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ይሁን ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድ ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም።
እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳት በመጉዳት አይወገድምና።
ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰዎችን ለሚጎዳ ሰው ጉዳት እንደሚያገኘው፤ ሰዎችን ለሚያጨናንቅም መጨናነቅ እንደሚያገኘው ዛቱ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከማመሳሰል (ከደረሰበት በደል) በበዛ መልኩ መበቀል መከልከሉን እንረዳለን።
  2. አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም።
  3. በንግግር ወይም በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን አውቆም ይሁን ሳያውቁ መጉዳት ተከልክሏል።
  4. ምንዳ በስራው አይነት ነው የሚሰጠው። የጎዳ ሰው አላህ ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀም አላህ ያጨናንቀዋል።
  5. ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ