+ -

عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ بُسْرٍ رضي الله عنه أَنَّ رَجُلاً قَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ إِنَّ شَرَائِعَ الإِسْلاَمِ قَدْ كَثُرَتْ عَلَيَّ، فَأَخْبِرْنِي بِشَيْءٍ أَتَشَبَّثُ بِهِ، قَالَ:
«لاَ يَزَالُ لِسَانُكَ رَطْبًا مِنْ ذِكْرِ اللَّهِ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 3375]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ቡስር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእስልምና ድንጋጌዎች በርግጥም በኔ ላይ በዙብኝ። አጥብቄ የምይዘውን አንዳች ነገር ይንገሩኝ።" እርሳቸውም እንዲህ አሉ:
"ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3375]

ትንታኔ

አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከደካማነቱ አንፃር ግዴታ ያልሆኑ አምልኮዎች እስኪያቅቱት ድረስ መብዛታቸው እንደተሰማው ስሞታ አቀረበ። ቀጥሎም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብዙ ምንዳ የሚያመጣለት የሆነን አጥብቆ የሚይዘውን ቀላል ስራ እንዲጠቁሙት ጠየቀ።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታና ወቅት ምላሱ በ"ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ በ"ተሕሚድ" (አልሐምዱሊላህ)፣ ምህረት በመጠየቅ (አስተጝፊሩሏህ)፣ ዱዓ በማድረግና በመሳሰሉት አላህን በማውሳት ዘውትሮ ምላሱን ማንቀሳቀስና ማርጠብ እንዳለበት ጠቆሙት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህን በማውሳት ላይ መዘውተር ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
  2. ከአላህ ችሮታ መካከል ትልቁ የምንዳን ምክንያት ማቅለሉ ተጠቃሽ ነው።
  3. ባሮች በበጎና መልካም እጣ ፈንታቸው እንደሚበላለጡ እንረዳለን።
  4. እንደ "ሱብሐነላህ"፣ "አልሐምዱሊላህ"፣ "ላኢላሃ ኢለላህ"፣ "አላሁ አክበር"ና ከዚህም ውጪ ያሉ አዝካሮችን ከቀልብ ጋር በማስተሳሰር በምላስ አላህን አብዝቶ ማውሳት የብዙ ግዴታ ያልሆኑ (ሱና) አምልኮዎችን ደረጃ ይይዛል።
  5. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሁሉም ጠያቂዎች የሚስማማቸውን መልስ እየጠበቁ መመለሳቸውን እንረዳለን።