عن أبي هريرة رضي الله عنه:
أَنَّ رَجُلًا قَالَ لِلنَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: أَوْصِنِي، قَالَ: «لَا تَغْضَبْ» فَرَدَّدَ مِرَارًا قَالَ: «لَا تَغْضَبْ».

[صحيح] - [رواه البخاري]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ:
አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት።

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

ከሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና አንዱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ የሚጠቅመውን ነገር እንዲጠቁሙት ፈለገ። እርሳቸውም እንዳይቆጣ አዘዙት። ይህም ማለት ወደቁጣ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን እንዲርቅ፣ የሚያስቆጣ ነገር በተከሰተ ጊዜም ነፍሱን እንዲቆጣጠር፣ በቁጣው ወደ መግደል፣ መማታት፣ ስድብና የመሳሰሉት ነገር እንዳይሻገር ማለት ነው።
ሰውዬውም በተደጋጋሚ ምክር እንዲጨምሩለት ፈለገ። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አትቆጣ!" ከምትለው ምክር የዘለለ ምንም አልጨመሩለትም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከቁጣና መንስኤዎቹ መጠንቀቅ እንደሚገባ፤ ቁጣ የክፋት መሰብሰቢያ ነው። ከሱ መጠበቅ የመልካም መሰብሰቢያ ነው።
  2. ለአላህ ብሎ መቆጣት የአላህ ክልከላዎች ሲደፈሩ መቆጣትን ይመስል ምስጉን የሆነ ቁጣ ነው።
  3. ሰሚው እስኪሸመድደውና አንገብጋቢነቱን እስኪገነዘብ ድረስ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ንግግርን መደጋገም እንደሚገባ፤
  4. አዋቂ ከሆነ ሰው ምክር መፈለግ ያለውን ትሩፋት ተረድተናል።