عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا تَحَاسَدُوا، وَلَا تَنَاجَشُوا، وَلَا تَبَاغَضُوا، وَلَا تَدَابَرُوا، وَلَا يَبِعْ بَعْضُكُمْ عَلَى بَيْعِ بَعْضٍ، وَكُونُوا عِبَادَ اللهِ إِخْوَانًا الْمُسْلِمُ أَخُو الْمُسْلِمِ، لَا يَظْلِمُهُ وَلَا يَخْذُلُهُ، وَلَا يَحْقِرُهُ التَّقْوَى هَاهُنَا» وَيُشِيرُ إِلَى صَدْرِهِ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ «بِحَسْبِ امْرِئٍ مِنَ الشَّرِّ أَنْ يَحْقِرَ أَخَاهُ الْمُسْلِمَ، كُلُّ الْمُسْلِمِ عَلَى الْمُسْلِمِ حَرَامٌ، دَمُهُ، وَمَالُهُ، وَعِرْضُهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2564]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ። ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለው፤ እርዳታ አይንፈገው፤ አያሳንሰው።" ወደ ደረታቸው እየጠቆሙም ሶስት ጊዜ "አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው።" አሉ። "ሰውዬው ሙስሊም ወንድሙን አሳንሶ መመልከቱ መጥፎ ሠራ ለመባል ይበቃዋል። ሁሉም ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ደሙ፣ ገንዘቡና ክብሩ እርም ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2564]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሙስሊም የሆነ ሰው ለሙስሊም ወንድሙ መልካም እንዲሆን መከሩ። የተወሰኑን በርሱ ላይ ግዴታ የሆኑ ነገሮችን፣ ስነስርዓቶችንና የመሳሰሉትንም ነገሮች ገለፁ። ከነዚህም መካከል: የመጀመሪያው ምክር: አትመቀኛኙ! ይሀውም አንዳችሁ የአንዳችሁ ፀጋ እንዲወገድ መመኘቱ ነው። ሁለተኛው: መግዛቱን ሳይፈልግ ሻጩን ለመጥቀም ወይም ገዢውን ለመጉዳት አስባችሁ የሸቀጡን ዋጋ በመጨመር ለማስወደድ አትጫረቱ! ሶስተኛው: አትጠላሉ! ይህም ማለት መጎዳቱን መፈለግ ነው። ይህም የውዴታ ተቃራኒ ነው። ነገር ግን ጥላቻው ለአላህ ከሆነ የዛኔ መጥላቱ ግዴታ ይሆናል። አራተኛው: ጀርባ አትሰጣጡ! ይህም አንዳችሁ ለወንድሙ ጀርባውን መስጠቱ፤ ከርሱም መዞሩና ማኩረፉ ነው። አምስተኛው: አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! ይህም ሸቀጥን ለገዛው ሰውዬ "እኔ ዘንድ ይህን እቃ የመሰለ በርካሽ ዋጋ አለ" ወይም "በዚሁ ዋጋ ከዚህ የተሻለ ሸቀጥ አለ።" ማለቱ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ በማለት ጠቅላይ የሆነ ምክርን መከሩ፡ የጠቀስኩላችሁን ክልከላዎች በመተው፤ ውዴታን፣ እዝነትን፣ ርህራሄንና ገርነትን በመስጠት፤ በመልካም ነገር ላይ በመተጋገዝ፤ ቀልብን ከማፅዳትና በማንኛውም ሁኔታ ከመመካከር ጋር "እንደ ወንድማማቾች ሁኑ"። ይህን ወንድማማችነት ከሚያስፈርዱ ነገሮች መካከልም: ሙስሊም ወንድሙን አለመበደልና በርሱ ላይ ወሰን አለማለፍ፤ ሙስሊም ወንድሙ ግፍ እየተሰራበት መርዳት በሚችልበት ቦታና ከርሱ ላይ ግፉን ማስወገድ በሚችልበት ቦታ እርዳታ በመንፈግ ሙስሊም ወንድሙን አይተወው፤ ሙስሊም ወንድሙን አለማሳነስና በወረደና በዘቀጠ እይታ አለመመልከት ነው። ይህም የቀልብ ውስጥ ኩራት ውጤት ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህን መፍራት ቀልብ ውስጥ እንደሆነ ሶስት ጊዜ ገለፁ። መልካም ስነምግባርን፣ አላህን መጠንቀቅንና አላህን መጠባበቅን የምታስፈርደው አላህን መፍራት ቀልቡ ውስጥ ያለበት ሰው ሙስሊምን አያሳንስም። ሙስሊም ወንድሙን ማሳነሱ መጥፎ ነገርና የዘቀጠ ስነምግባር ላይ መሆኑን ለማሳየት በቂ ነው። ይህም ቀልቡ ውስጥ ኩራት ስላለ ነውና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀደም ብለው የተናገሯቸውን ነገሮች የሚያጠናክር ነገር ተናገሩ። ሁሉም ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ ደሙ ማለትም በመግደል ወይም ከዛም ውጪ እንደማቁሰል ወይም መምታትና የመሳሰሉት በሆነ ነገር ወሰን ማለፉ ሐራም ነው። ልክ እንደዚሁ ገንዘቡም ሐራም ነው። ይህም ያለአግባብ ገንዘቡን መውሰዱ ነው። ልክ እንደዚሁ ክብሩም ሐራም ነው። ይህም ራሱን ወይም ዘሩን ማነወር ነው።