+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: أَخَذَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِمَنْكِبِي، فَقَالَ:
«كُنْ فِي الدُّنْيَا كَأَنَّكَ غَرِيبٌ أَوْ عَابِرُ سَبِيلٍ»، وَكَانَ ابْنُ عُمَرَ، يَقُولُ: إِذَا أَمْسَيْتَ فَلاَ تَنْتَظِرِ الصَّبَاحَ، وَإِذَا أَصْبَحْتَ فَلاَ تَنْتَظِرِ المَسَاءَ، وَخُذْ مِنْ صِحَّتِكَ لِمَرَضِكَ، وَمِنْ حَيَاتِكَ لِمَوْتِكَ.

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6416]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትከሻዬን ያዙኝና እንዲህ አሉ:
"በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።" ኢብኑ ዑመርም እንዲህ ይል ነበር "ስታመሽ ንጋትን አትጠብቅ፣ ስታነጋ ምሽትን አትጠብቅ፣ በጤንነትህ ለበሽታህ ስንቅ ያዝ፣ በህይወትህ ለሞትህ ስንቅ ያዝ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6416]

ትንታኔ

ኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትከሻውን ያዙና እንዲህ አሉት: በዱንያ ውስጥ ስትኖር ከፈጣሪ ጋር ከመጠመድ ያዘናጉ ከነበሩ ግንኙነቶች፣ ከቤተሰቡና ከዘመዱ ተገልሎ የሚያስጠጋው ቤት ወደሌለበትና የሚጠብቀው ነዋሪ ወደሌለበት ሀገር እንደገባ እንግዳ ሁን፤ እንደውም ከእንግዳም የባሰ ሁን። ይሀውም ሀገሩን ፍለጋ በመንገድ እንደሚያልፍ መሆን ነው። ምክንያቱም እንግዳ የሆነ ሰው ሀገሩ መግባት አስቦ መንገድ ከጀመረው ሰው በተቃራኒ በእንግድነት ባረፈበት ሀገር ተረጋግቶ ይቀመጣልም ያሳልፋልም። የመንገድ ተጓዥ ባህሪ ግን ነገሮችን ማቅለል፣ መጓዝን አለመተውና ወደ ሀገሩ ለመድረስ በጉጉት መጣር ነው። ተጓዥ የሆነ ሰው ሀገሩ ከሚያደርሰው ነገሮች ውጪ ተጨማሪ ነገር እንደማይፈልገው ሁሉ ልክ እንደዚሁ አንድ አማኝ በዱንያ ውስጥ ሲኖር ወደ አላማው ስፍራ ከሚያደርሰው ነገር ውጪ ተጨማሪ ነገሮችን አይፈልግም።
ኢብኑ ዑመርም ይህን ምክር በመመርኮዝ እንዲህ ይል ነበር: ያነጋህ ጊዜ ምሽትን አትጠብቅ፤ ያመሸህ ጊዜ ንጋትን አትጠብቅ፤ ነፍስህን የቀብር ነዋሪ አድርገህ ቁጠራት፤ እድሜ ከጤናና በሽታ አያገልምና። ለበሽታ ዘመንህ ስንቅ ሊሆንህ ዘንድ የጤንነትህን ዘመን በአምልኮ ተቻኮልባት፤ ባንተና በጤንነት መካከል በሽታ ከመጋረዱ በፊት በጤንነት ዘመንህ መልካም ስራዎችን ሸምት፤ የዱንያ ህይወትህን ሸምትባት፤ ከሞት በኋላ የሚጠቅምህን ነገር ዱኒያ ላይ ሳለህ ሰብስብ!

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አስተማሪ የሆነ ሰው በማስተማር ወቅት ፈታ ለማድረግና ለማንቃት እጁን በተማሪው ትከሻ ላይ ማድረግ እንደሚቻል እንረዳለን።
  2. ምክርና ጥቆማ እንዲሰጠው ላልጠየቀ ሰው እንኳ በምክርና ጥቆማ መጀመር እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  3. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አሳማኝ ምሳሌን በመጥቀስ የማስተማር ስልታቸው ማማሩን እንረዳለን። ይህንንም "በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።" ከሚለው ንግግራቸው የምንረዳው ነው።
  4. ሰዎች ወደ መጪው አለም ባላቸው ጉዞ እንደሚለያዩ እንረዳለን። በዱንያ ጉዳይ ቸልተኛ ከመሆን አንፃር እንደ እንግዳ ከሆነ ሰው ይልቅ እንደ መንገድ አላፊ የሆነ ሰው የበለጠ ቸልተኛ ነው።
  5. ምኞትን ማሳጠርና ለሞት መዘጋጀት መገለፁን እንረዳለን።
  6. ሐዲሡ ከዱንያ ቸልተኛ መሆንንና ዱኒያን ማሳነስን ይጠቁማል እንጂ ሲሳይን መተውና የዱንያን ጥፍጥና መከልከሉን አይጠቁምም።
  7. መልካም ስራ የመስራት አቅምን ከማጣትና በበሽታ ወይም በሞት ከመጋረድ በፊት መቻኮል እንደሚገባ እንረዳለን።
  8. ዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዚህ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምክር ተፅእኖ ስር መውደቁ የርሱን ደረጃ ያስረዳናል።
  9. የአማኞች ሀገር ጀነት ናት። አማኝ ሰው በዱንያ ውስጥ እንግዳ ነው። ጉዞውም ወደ መጪው ሀገር ነው። ቀልቡን በእንግድነት ሀገር ውስጥ በአንዳችም አያንጠለጥልም። ይልቁንም ቀልቡ ወደ ሚመለስበት ሀገር የተንጠለጠለ ነው። በዱንያ ውስጥ ያለው ቆይታ ጉዳዩን ለማስፈፀምና ወደ ሀገሩ ለመመለስ የመሰናዳት ያህል ነው።