+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«كُلُّ سُلاَمَى مِنَ النَّاسِ عَلَيْهِ صَدَقَةٌ، كُلَّ يَوْمٍ تَطْلُعُ فِيهِ الشَّمْسُ يَعْدِلُ بَيْنَ الِاثْنَيْنِ صَدَقَةٌ، وَيُعِينُ الرَّجُلَ عَلَى دَابَّتِهِ فَيَحْمِلُ عَلَيْهَا أَوْ يَرْفَعُ عَلَيْهَا مَتَاعَهُ صَدَقَةٌ، وَالكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ، وَكُلُّ خُطْوَةٍ يَخْطُوهَا إِلَى الصَّلاَةِ صَدَقَةٌ، وَيُمِيطُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ صَدَقَةٌ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2989]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው። ፀሀይ በምትወጣበት ቀናት ሁሉ፤ በሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅ ምፅዋት ነው። ሰውዬውን መጓጓዣው ላይ እንዲወጣ ማገዝ ፣ እርሷ ላይ ማሸከም ወይም እቃውን እርሷ ላይ መጫን ምፅዋት ነው። መልካም ንግግር ምፅዋት ነው። ወደ ሶላት የሚራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ነው። ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድ ምፅዋት ነው።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2989]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁሉም ቀን በሁሉም ለአቅመ አዳም በደረሰ ሙስሊም ላይ ሁሉ በመገጣጠሚያ አጥንቶቹ ቁጥር ያህል ለሰጠው ጤንነት ለማመስገንና አጥንቶቹን መጨበጥና መዘርጋት በሚችል መልኩ ስለገጣጠመው ለአላህ ብሎ መመፅወት እንደሚገባው ገለፁ። ይህቺም ምፅዋት በመልካም ተግባራት ባጠቃላይ እንደሚፈፀምና ገንዘብ በመስጠት ላይ ብቻ እንዳልታጠረ ገለፁ። ከነርሱም መካከል: በተጣሉ ሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅና መፍረድ ምፅዋት ነው። መጓጓዣው ላይ ለመውጣት ለተሳነው ሰውዬ በማሰቀልህ ወይም እቃውን በመጫን ማገዝህ ምፅዋት ነው። ዚክር፣ ዱዓ ማድረግ፣ ሰላምታ ማቅረብና ሌሎችም መልካም ንግግሮች ምፅዋት ናቸው። ወደ ሶላት የምትራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ናት። መንገድ ላይ የሚያውክን ነገር ማስወገድም ምፅዋት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰው ልጅ አጥንቶች ተገጣጥመው መሰራታቸውና የነርሱም ደህና መሆን ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎች መካከል እንደሆነ እንረዳለን። ለያንዳንዱ ፀጋ የሚያቀርበው ምስጋና እንዲሞላም ለሁሉም አጥንት መመፅወት አስፈላጊ ነው።
  2. ይህ የአላህ ፀጋ እንዲዘወትርም ምስጋናን በየቀኑ በማደስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. በየቀኑ ግዴታ ያልሆኑ ስራዎችን በመስራትና ምፅዋት በማድረግ ላይ በመዘውተር መነሳሳቱን እንረዳለን።
  4. በሰዎች መካከል ማስታረቅ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
  5. ወንድምን በማገዝ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም ወንድምን ማገዝ ምፅዋት ስለሆነ ነው።
  6. የጀመዓ ሶላት በመገኘት ላይ፣ ወደርሱ በመሄድ ላይና መስጂድን በዚህ በማሳመር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  7. ሙስሊሞች የሚያውካቸውንና የሚጎዳቸውን ነገር በማራቅ የሙስሊሞችን መንገድ ማስከበር ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።